#የታይታኒክ_ባልንጀራ
ዛሬ የዝነኛዋ ታይታኒክ መርከብ ስትሰጥም የተወለዱትን የ112 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው ሰው ታሪክ ለግርምታችን እናወሳለን።
ዝነኛዋ ታይታኒክ መርከብ በሰመጠችበት ዓመት የተወለዱት የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋ ጆን አልፍሬድ ቲኒስዉድ 112ኛ ዓመት ልደታቸውን በእንግሊዝ በሚገኝ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ማዕከል ባለፈው የፈረንጆቹ ነሐሴ ወር አክብረዋል።
ጆን አልፍሬድ ቲኒስዉድ የተወለዱት እ.ኤ.አ ነሐሴ 26 1912 በሊቨርፑል ከተማ ሲሆን ይህም ዝነኛዋ የታይታኒክ መርከብ ከሰመጠች ከአራት ወራት በኋላ ነበር።
በያዝነው ዓመት መጀመሪያ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ በዓለማችን ላይ ካሉ ወንድ ሰዎች ሁሉ በዕድሜ ትለቁ ለመሆናቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ረጅም እድሜ ለመኖራቸው ምስጢሩን ሲጠየቁም “ምንም የተለየ ምስጢር የለውም፣ እንዴት እንደሆነ አላውቀውም” ብለዋል።
ወጣት እያሉ ብዙ የእግር ጉዞ ያደርጉ እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያዘወትሩ እንደነበር የተናገሩት ጆን ቲኒስውድ “ነገር ግን ከሌሎች የተለየ ያደረግኩት ነገር የለም” ማለታቸውን ዩፒአይ አስነብቧል።
በአሁኑ ወቅት የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋዋ ሰው ጃፓናዊቷ ቶሚኮ ኢቶካ ሲሆኑ በዚህች ምድር ላይ 116 ዓመታትን ኖረዋል።
(ጋሸ ጆን አልፍሬድ ቲኒስዊድ ፀሎት ሲያደርጉ "ጌታ ሆይ እድሜዬን ጨምርልኝ" ይሉ ይሆን?
_______