"እስር ቤት ስለሆንክ ብቻ እስረኛ ነህ ማለት አይደለም"
ሪኪ ገና የ18 ዓመት ልጅ ሳለ ባልፈጸመው ወንጀል ምክንያት የሞት ፍርድ ተበየነበት። ለ39 ዓመታት ያህል እስር ቤት ውስጥ ማሰብ የሚከብድ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ በመጨረሻ ነጻ ሆነ፤ ሆኖም በፍትሕ መጓደል ምክንያት በእስር ቤት ላሳለፋቸው ዓመታት ዳጎስ ያለም ካሳ ተከፈለው።
ሪኪ ከእስር ከተፈታ በኋላ በእስር ቤት እንዲገባ ምክን ያት ከሆነውን ሰው ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጡ ። በአስገራሚ ሁኔታ አቀፈውና "ይቅር ብዬሃለሁ" አለው።
ሪኪ በቃለ መጠይቅ ላይ "እስር ቤት ስለሆንክ ብቻ እስረኛ ነህ ማለት አይደለም" ሲልም ተናግሯል። እውነተኛ ነፃነት የሚገኘው ከውስጥ እንደሆነ ጠቅሷል ። ሕይወት ሰፊ፣ ብዙ ገጽታ ያለው ጉዞ እንደሆነ በማስታወስ ቂምና ጥላቻን መተው እንዳለብንም ገልጿል።
ይቅር ባይነት ለራሳችን የምንሰጥ ውድ ስጦታ ነው ብሎ ያምናል። ይቅርታ ማድረግ ማጣት ሳይሆን፤ ፍቅርን ማሳደግ፣ መልካምነት መገንባት፣ መንፈሳችንን ማደስ ነው ብሎ ያምናል።
ሁላችንም ልባችን ይቅርታን እንዲፈልግ እና ሌሎችን ይቅር ለማለት የሚያስችል ጥበብ ለማግኘት ጥረት እናደርግ ሲልም መል እክቱን አስተላልፏል።
ያለፈ ታሪካችን እስረኞች አንሁን፤ ይልቁንም ነገ የሚያመጣልንን ገደብ የለሽ አማራጮችን እንመልከት!
@Amazing_fact_433