✨✨ሁለት ራስ✨✨
"ወንድነቱን ተፈታተንኩት....".....አለችኝ ደንደን ብላ እየተቀመጠች....
"እንዴት...."...አልኳት ለመልሷ ጓጉቼ...
"provide እንዲያደርግ አልፈቀድኩለትም....protector እንደማያስፈልገኝ አሳየሁት...ገብቶሻል የምልሽ እኔ ለራሴ እንደምበቃ በተዘዋዋሪ ነገርኩት....ወንድነቱን ቀማሁት...."
"ለራስሽ መሆንሽ እኮ ደስ ሊለው ይገባ ነበር...."...አልኳት
"አይምሰልሽ....ወንድ ልጅ በተፈጥሮው protector or provider መሆን ያስደስተዋል....እኔ በጣም independent ስሆን አላስፈላጊነት ተሰማው....አልፈርድበትም ተፈጥሮው ነው....እርሱም አይፈርድብኝም የኖርኩት ህይወት በማንም ላይ እንዳልመረኮዝ አድርጎ ሰርቶኝ ነው....
ታውቂያለሽ ልጋብዝሽ ብሎኝ ተገናኝተን ካልከፈልኩ ራሴን እንደሚያመኝ.....
ተሳስቶ ፀጉርሽን ላሰራሽ እንዳይለኝ በየሳምንቱ በምቀያይረው human hair ለራሴ እንደምበቃ አሳየዋለሁ....ልብሴን በቀን ሁለቴ ስቀይር ፊቱ ላይ ድንጋጤውን አየዋለሁ....ቋሚ ጠረን እንኳን የለኝም....ሽቶ እየቀያየርኩ አፍ ሳይወጣኝ በጠረኔ ብቻ ለራሴ በቂ ነኝ እለዋለሁ.....
ለመጀመሪያ ጊዜ መኪናው ውስጥ እንድገባ በኩራት ሲጋብዘኝ ወደ መኪናዬ ጠቁሜው ምግብ የምንበላበት ቤት እንዲከተለኝ ስነግረው ኩራቱ ሲረግብ በአይኔ አይቼዋለሁ....."
"መጨረሻ ላይ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ"
" 'ራሴን የማግባት እቅድ የለኝም'....ብሎኝ ነው የሄደው....ተፈጥሮን አትጋፊውም....ልክ አልነበርኩም....ሌላው ቀርቶ አለሁልሽ እንዲለኝ እንኳን ፈቅጄለት አላውቅም...ማልቀስ ብፈልግ እንኳን በሬን ዘግቼ ነው የማለቅሰው....ለአመታት ያለከልካይ ሳነባ እርሱ አያውቀኝም....አይዞሽ ለመባል ድምፄን ጮክ አድርጌ ሳለቅስ እርሱ አያውቀኝም....አየሽ እዚች ጋር ተላለፍን....
ወንድ የቤት ራስ አይደል....ሴት ደግሞ ሰውነት....ራስ ያለ ቀሪው ሰውነት...ከአንገት በታች ያለውም ሰውነት ያለ ራስ ምንም ናቸው...ሁለት ራስ ቢኖር ያለሰውነት ምንድን ነው....?....አየሽ ሁሉም የተሰጠውን character በአግባቡ ሲጫወት ነው ተውኔት የሚያምረው.....ልክ አልነበርኩም....የኖርኩት ህይወት ልክ ባልሆነ መንገድ ሰራኝ"
"ህመም አሞ ብቻ ቢተው ጥሩ ነበር....በታመምሽው በኩል አጥር ስታበጂ ትኖርያለሽ....ከዛ የሆነ ቦታ ላይ ራስሽን ከራስሽ ጋር ብቻ ታገኝዋለሽ"....
የምላት አጣሁ....ራስን ከራስ ጋር ብቻ ማግኘት ስሜቱ ምን ምን ይል ይሆን...እንጃ ።
✍Shewit