ኮስታራ ናት እንኳን ገና ላልቀረበቺው ቀርቶ ለቀረቧትም ፊቷ አይፈታም።ጭምት ናት።ለሰዎች ደግ እና ቁምነገረኛ መሆኗን ግን ብዙ ሰው ይስማማበታል።እኔ ደግሞ ጥሎብኝ ኮስታራ ሰው እወዳለሁ፤ምንም እንኳን ሳቂታ ብሆንም...ለምንም ነገር ሳቅ ይቀድመኛል...ስናደድ እንኳን እስቃለሁ።
"ያለ ሳቅ ህይወት ምንድነው?" ብዬ የማስብ አይነት ሰው ነኝ።
የእሷ ህይወት?
ሳቅ ፈፅሞ የማይታወቅበት ጨለማ ነው ብዬ ደመደምኩ...የማስፈልጋት መስሎ ተሰማኝ...ለጨለመ ህይወቷ ጭላንጭል ብርሃን ልሆን...ፋኖሴን ይዤ ቀረብኳት፥ፈገግታዬን።
አልገርምም?
ማን ነኝ ብዬ ነው የማስበው?
የመጀመሪያ ሰሞን በቀልድ የተከሸኑትን ረጃጅም አረፍተ ነገሮች...በአጭር መልስ ድባቅ መትታ ጨዋታ ታስጠፋብኝ ነበር።እንኳን ለማሳቅ በወጉ ለማውራትም ቃላት እያጠረኝ መጣ...ይቺ ሴት ፋኖሴን፥ፈገግታዬን እፍ ብላ አጥፍታ እኔንም ያለሳቅ ልታስቀረኝ ነው?
እሷን ሳያት "በፌዘኞች ወንበር አትቀመጥ" የሚለውን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታውሰዋለው...በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች ላስቃት ስውተረተር፣ቃላት ጠፍቶብኝ ስደናበር...ርቃኝ ልደርስባት ስንጠራራ...በቀልዶቼ ሳይሆን በሁኔታዬ ፈገግ ማለት ጀመረች...ኋላ ላይ ሁኔታዬ አሳዝኗት ነው መሠል እሷው ታስቀኝ ጀመር...
አልፎ አልፎ እንደ ቅመም ጣል የምታደርጋቸው ቀልዶቿ ሆዴን አስይዘው ያስቁኛል...በሳቄ እሷ ትስቃለች...ሳቋ ደስ ይለኛል...ሳቋን ለማየት አንዳንዴ እንዲሁ እገለፍጣለሁ።
አንድ ቀን ብዙ ግርግር በማይበዛበት እሷ ባሳየቺኝ ካፌ ቁጭ ብለን ስንጨዋወት..."ከሳቅ ያኳረፈሽ ምንድነው?" ብዬ ጠየኳት።መልሱን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳ መላ አካላቴ ጆሮ የሆነ እየመሰለኝ።
ጥያቄን በጥያቄ መለሠች። " ሰው ስለሳቀ ደስተኛ ነው ማለት ነው? " አለቺኝ በአይኖቿ ትኩር ብላ እየተመለከተቺኝ።
"ይመስለኛል...ሳቅ የደስታ መገለጫ አይደል፤እንባ ደግሞ የሐዘን።" አልኳት።
"ሐሴት ምን እንሆነ ታውቃለህ?" አለቺኝ።
"ደስታ አይደል"አልኳት በጥርጣሬ።
"አዎ ነው ግን ምን አይነት ደስታ?" ዝም አልኳት ግራ መጋባቴን አይታ ቀጠለች።
"ውስጣዊ ደስታ!" አለችና እርካታ የተሞላበት ፈገግታ ተጎናፀፈች...ሐሴት አደረገች?
ማብራሪያዋን ቀጥላለች "...ሐሴት ማለት ከትክክለኝነት የሚመነጭ ደስታ ነው...አደርገዋለሁ ያልከውን ስታደርገው ነኝ ያልከውን ስትሆን...ብዙዎቹን የራቀው ደስታ ይሄ ነው...እኔ ደስ እንዲለኝ...በየማዕበራዊ ገፁ የሚያሥቅ ነገር ሳስስ ውዬ አላውቅም...ውጪያዊ ደስታ ውሥጥን አርክቶ አያውቅም፤ይልቅ ባዶነት እንዲሠማህ ያደርጋል አንዳንዴም...ሰዎች ደስታ ውስጣቸው እንዳለ ዘንግተውት ደስታን ፍለጋ አይሆኑ ሲሆኑ ያሳዝኑኛል።እኔ ምንም እንኳን ባልስቅም ውስጤ ባለው ሰላም ሐሴት አደርጋለሁ። "
አለች ፍፁም መረጋጋት እና ስክነት ከሁናቴዋ እያነበብኹ።
ከተለያየን ፤ ከሄደች በኋላ ራሴን ጠየቅኹ...
እውነት ደስተኛ ነኝ?
እንጃ!
እኔም ብሎ ፋኖስ ለኳሽ፤ብርሃን አብሪ
እፍፍፍፍፍ....ፋኖሴን(ፈገግታዬን) አጠፋዋት!
ደግሞ ለፀሐይ የፋኖስ ብርሃን ምኗ ነው?
ለካ ጨለማ የነበረው የእኔ ህይወት ነው።
ከተቀደደው ማስታወሻ
©ሶፊ