ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል አንድ ብርቱ መምህር አለች።
ከተማሪዎቿ አንዱ አያወራም፣ ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም፣ ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው፣ ክፍል ውስጥ አይሳተፍም መምህቷም በዚህ ተማሪ ደስተኛ አይደለችም።
መምህርቷ የተማሪዎችን የቤት ሥራ እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የዚህ ተማሪ ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትጽፍ ሆነች በፍጹም አልወደደችውም።
በትምህርት ቤቱ ሕግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ ዓመታት የውጤት ፋይሎችን አሁን ያሉ መምህራኖች ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርቷ ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል ዓይታ የዚሁ ተማሪ መጨረሻ ላይ ቀረ።
መምህርቷ የተማሪውን ውጤት አነበበችው ተገረመችም ደነገጠችም...!
የአንደኛ ክፍል መምህሩ "በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው" ሲል ሀሳብን አስፍሯል።
የሁለተኛ ክፍል መምህሩም " ጎበዝ ተማሪ ነው ነገር ግን በዚህ ዓመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል"ሲል ጽፏል።
የሶስተኛ ክፍል መምህሩ ደግሞ " በእናቱ ሞት ተጎድቷል! አባቱም በሀዘን ስለተጎዳ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም" ሲል ስለተማሪው ጽፏል።
የአራተኛ ክፍል መምህሩም "አባቱን በሞት የተነጠቀው ይህ ተማሪ ብቸኛ ነው ከማንም ጋር አያወራም ውጤቱም በጣም ወርዷል"ሲል ጽፏል።
እለቱ የገና ዋዜማ ነው ተማሪዎች ለመምህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት ዕለት ነው ሁሉም ተማሪዎች ለመምህራቸው የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር።
በስተመጨረሻ ይህ በትምህርት ደካም እና ጎስቋላ የሆነው ተማሪ መጣ...
በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል...
...የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር።
የክፍሉ ተማሪዎች ይህንን ዓይተው ሳቁ መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው ሽቶውን ተቀባች ተማሪውንም አቀፈችው።
"ዛሬ እናቴን መስለሻል... እናቴን እናቴንም ሸተሻል" አላት እንባ እየተናነቀው...
መምህርቷ ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰዓታት ብቻዋን አለቀሰች።
...ከዚያ ግዜ ጀምሮ መምህቷ ተማሪውን በሚገባ ተከታተለችው እርሱም አላሳፈራትም ጎበዘ ሆነ ትምህርቱንም በትኩረት ይከታተል ያዘ።
...ዓመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ።
በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራኖቹ ተመራጭ እና ለብዙ ተማሪዎች ምሳሌ ሆነ ...
በፀባዩም ምስጉን፣በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እንዲሁም ደስተኛ ሆነ።
መምህርቷም ሁልግዜም ዓለምን የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግኝ እርሱ ነው ስትል ትናገራለች
✨ እንማር