የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅም ሆነ!
የጌታ ልደት ረቂቅ ነው። በፍጥረት ታሪክ ከሆኑ ክንውኖች አምላክ ሰው የሆነበት ክስተት እጅግ ድንቁ ነው። ይኽን ግዙፍ አጽናፍ የፈጠረ ከመታወቅ ያለፈው ምጡቁ፥ አምላክ በፈቃዱ ሰው ሆነ(ዮሐ 1፥14 ፣ ፊሊ 2)። ብርቱው አምላክ በፈጠው ደካማ ፍጥረት እጅ ለመሞት ፈቃደኛ ኾነ። በማንም ሊቀረብ የማይችል አምላክ በደካማይቱ ማህጸን ለመጸነስ በቃ። ይኽን እውነት እንድናውቅ ጸጋውን ያበዛልንን እግዚአብሔር እንዴት ልናመሰግን ይገባ ይኾን?
የኾነው ሆኖ አምላክ ሰው ስለሆነበት ረቂቅ ሚስጥር ለማውራት አይደለም መነሻዬ። ጌታ ኢየሱስ ከተወለደበት አበይት አላማ መካከል አንዱን እንድናነሳ ወድጃለሁ። ጌታ ብዙ ነገር ሆኖልናል ከዚህ ውስጥ ክብሩን በመተው ሰው የሆነበት እውነት አንዱ ነው(ዮሐ 1፥14፣ ፊል )። በአንድ ወቅት በአምላክ መኖር ማያምን የነበረው ባለአእምሮ የስነ ጽሁፍ ምሁሩ ሲ.ኤስ. ሌውስ "የሰው ልጆች የአምላክ ልጆች እንዲሆኑ ያስችል ዘንድ የአምላክ ልጅ የሰው ልጅ ኾነ።"* ማለቱ ይታወሳል። ወላጅ አልባ አልነበርንም አስቀድሞ የማን ልጆች እንደነበርን ይታወቃል።
ከክንዱ ማንም ከማያስመልጠን በኃያሉ አምላክ ቁጣ ስር ስለነበርን መጽሐፍ "ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን" ይለናል(ኤፌ 2፥3) ለዚህም ነው አሁን እንኳን በኢየሱስ በማያምን ላይ "የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም" የሚለን(ዮሐ 3፥36)። "የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው። ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ከእግዚአብሔር አይደለም።"(1 ዮሐ 3፥10) እንደሚል ኃጢአትን እያደረግን እንደገዛ ፈቃዳችን እንመላለስ ስለነበር የጨካኙ ዲያብሎስ ልጅ ነበርን ማለት ይሆናል(ኤፌ 2፥1-5)። በግራም ነፈሰ በቀኝ አባታችን እግዚአብሔር አይደለም።
"የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ያስችል ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆነ!"፣ ጌታ ተወለደ ፣ የአለም መድኃኒት በበረት ግርግም ተወለደ፤ በዚህም ምክንያት በኢየሱስ አምነን የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ ስልጣን ተሰጥቶናል። "የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለ ፍቅር እንደሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን።" 1 ዮሐ 3፥1
የጌታን ልደት ስናስብ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያደረገውን ድንቅ ነገር እያሰበን ይሆን። የጌታን ልደት ስናስብ መድኃኒቱን ባለማወቃቸው እየጠፉ ያሉ አእላፍ ሕዝብ በመጸለይ ይሁን።
መልካም በአል!
*“The Son of God became a man to enable men to become sons of God." -C.S Lewis
Amanuel A.
©መንፈሳዊ መጽሐፍት