የቴኒስ ስፖርት የታዳጊዎች ፕሮጀክት ሥልጠና ለመጀመር ምክክር ተካሄደ
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአርባ ምንጭ ከተማ ታዳጊ ህጻናትን በቴኒስ ስፖርት ለማሰልጠን የሚረዳ ፕሮጀክት ለመጀመር ከኢትዮጵያ ቴኒስ ስፖርት ፌደሬሽን፣ ከጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ እንዲሁም ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ዘርፍ አካላት ጋር ታኅሣሥ 12/2017 ዓ/ም ምክክር አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ቴኒስ ስፖርት ፌደሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ከፈለኝ እንደገለጹት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ የሚሆነው ፕሮጀክት በቴኒስ ስፖርት የሰለጠኑ ታዳጊዎችን ከማፍራትና ሀገሪቱ በስፖርቱ የተሻለ እውቅና እንዲኖራት ከማስቻል አንጻር የራሱ ሚና ይኖረዋል። ፕሮጀክቱን ከማስጀመር አኳያ የባለድርሻ አካላት ተነሳሽነት የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት አቶ ይልማ የቴኒስ ስፖርት የሀገሪቱን ገጽታ በመገንባት፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ አንጻር እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሻሻል አንጻር ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን አመላክተዋል፡፡ የፌደሬሽን ጽ/ቤቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ባካሄደው ስምምነት መሠረት ለሚጀመረው ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍና ሙያዊ ሥልጠናዎች የሚሰጥ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡ አርባ ምንጭና አካባቢው በስፖርቱ ዘርፍ ምቹና ጠንካራ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቶሌራ የተናጥል ሥራን በማስቀረት በመተባበርና የተቀናጀ አሰራርን በመከተል በቴኒስ ስፖርት በUገር ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት ይሰራል ብለዋል፡፡
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር ተስፋዬ ገ/ማርያም እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በቴኒስ ስፖርት ብቁ የሆኑ ታዳጊዎችን ማፍራትን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ለፕሮጀክቱ ስኬት ባለድርሻ አካላት ከዩኒቨርሲቲው ጎን በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የስፖርት ሳይንስ መ/ርና ተመራማሪ እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አብርሃም ደርባቸው እንደገለጹት የቴኒስ ስፖርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ተወዳጅ ስፖርቶች መካከል አንዱ በመሆኑ በዘርፉ የሀገራቸውን ስም የሚያስጠሩ ታዳጊዎችን ለማፍራት ፕሮጀክቱ መቀረጹን አስርድተዋል ። አስተባባሪው አክለውም ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ታዳጊ ህጻናትን የመመልመል፣ የቴኒስ ስፖርትን አስመልክቶ የሥልጠና ማንዋሎችን የማዘጋጀትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን የመስጠት እንዲሁም ለስፖርቱ ምቹ የሆኑ መጫዎቻ ቦታዎችን የማመቻቸት እና መሰል ተግባራት በቀጣይ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
የጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ታመነ ተስፋዬ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለማኅበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚበረታቱና ምስጋና የሚቸራቸው መሆናቸውን ተናግረው ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት መምሪያው የሚቻለውን የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት