አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እንሰትን በዘመናዊ መልኩ ማዘጋጀት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጠ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት እና ከኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ለተወጣጡ እንሰት አምራች ኢንተርፕራይዞች እንሰትን በዘመናዊ መልኩ ማዘጋጀት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከታኅሣሥ 13-18/2017 ዓ/ም ድረስ ሰጥቷል፡፡
ሥልጠናው በእንሰት መፋቂያ፣ መፍጫና መጭመቂያ ማሽኖች አጠቃቀም፣ የእንሰት ምርት ጉድጓድ ውስጥ ሳይቀበር መብላላት በሚችልበት ዘዴ፣ የእንሰት እርሾ አጠቃቀም እና እንሰትን በተለያየ አይነትና መጠን ለምግብነት ማዘጋጀት ሥልጠናው የተሰጠባቸው አብይት ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ማኅበረሰብ ጉድኝትና ኢንደስትሪ ትስስር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር ተስፋዬ ገብረማርያም ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲው በበለጸጉ የእንሰት ቴክኖሎጂ ማሽኖች አጠቃቀም ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉና የዕውቀት ሽግግር በማካሄድ ሠልጣኞቹ ወደ አካባቢያቸው በመሄድ ማሽኖቹንና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሟቸው ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ከተመራማሪዎች ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር በምርምር የተገኙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለማኅበረሰቡ ለማዳረስ እየሰራ መሆኑንም ዶ/ር ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮ ቴክኖሎጂ መምህር፣ ተመራማሪና የእንሰት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር አዲሱ ፈቃዱ እንደገለጹት የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ እንሰት አብቃይ አካባቢ መሆኑና ማኅበረሰቡ እንሰትን ለምግብነት ለማዘጋጀትና ለገበያ ለማቅረብ የሚጠቀመበት ሂደት ባህላዊ አሠራርን የተከተለ በመሆኑ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ በሥልጠናው ከዞኑ ሁለት ወረዳዎች የተወጣጡ እንሰት አምራች እናቶችና ወጣቶች የተሳተፉ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አዲሱ ሠልጣኞች በባህላዊ አሰራሮች ምክንያት ሲፈጠሩ የነበሩ የጊዜ፣ የጉለበትና የምርት ብክነቶችን ከሚያስቀሩ ቴክኖሎጂዎች ጋር በተግባር እንዲተዋወቁ ተደርጓል፡፡ ዶ/ር አዲሱ የእንሰት ቴክኖሎጂን በስፋት ከማስተዋወቅና የማኅበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ በቀጣይ በሲዳማ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች መሰል ሥልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ባለሙያ ወ/ሮ አልማዝ ዘውዴ ኢንስቲትዩቱ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር እንሰት ላይ ያተኮሩ ምርምሮችን በትብብር አየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ ወ/ሮ አልማዝ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እንሰትን ለምግብነት የመጠቀም ልምድ አለመኖሩን ጠቅሰው፤ ኢንስቲትዩቱ ከአርባ ምንጭ፣ ከወልዲያና ከወሎ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ጋር ትብብር በመፍጠር በአካባቢው እንሰትን በስፋት ለማላመድ የሚያስችል አበረታች ሥራ እየተሰራ ነው፡፡
የኦሮሚያ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ባለሥልጣን የፕሮሰሲንግ ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ተመስገን ገዛኻኝ ባለሥልጣን መ/ቤቱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ባሻገር ሌሎች አካባቢዎችም የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራቱ የሚበረታታ ሲሆን መስሪያ ቤታቸው በመስኩ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አውስተዋል፡፡
የምዕራብ ሸዋ ዞን ሴቶችና ሕጻናት ጽ/ቤት ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ኢርባሳ እንደገለጹት ዞኑ በቆጮና ቡላ ምርት በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው መሆኑን ገልጸው በሥልጠናው የተዋወቁ ቴክኖሎጂዎች የምርት ጥራትን በማጎልበት ይበልጥ የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡
ከዞኑ ወንጪ ወረዳ የመጡት ሠልጣኝ ዳመነች ዓለሙ በሥልጠናው የተዋወቋቸው ቴክኖሎጂዎችና አዳዲስ አሰራሮች የእናቶችን የቆየ ድካም ከማስቀረት ባሻገር፣ የምግብ ጥራትን እንዲሁም ብክነትን የሚያስቀሩና ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሠልጣኟ ይህን ሥልጠና እንዲያገኙ ላመቻቹ አካላት በተለይ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ምስጋናቸው አቅርበዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት