የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ከሳውላ ካምፓስ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር ዉይይት እያካሄዱ ነው
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደቡ ከፍተኛ አመራሮች ከዩኒቨርሲቲው ሳውላ ካምፓስ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር የትውውቅና የውይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።
የውይይት መድረኩ በዩኒቨርሰቲው ቀጣይ ስትራቴጂክ አቅጣጫዎችና የሪፎርም አጀንዳዎች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ራስ ገዝ ከመሆን፣ ከመስክ ልይታ እና የልህቀት ማዕከል ዘርፍን ከመለየት አንፃር ለዩኒቨርሲቲው እንደ መንግሥት የተቀመጡ የሪፎርም አጀንዳዎች ፣ በቅርቡ ከትምህት ሚኒስቴር ጋር በተፈረመው የቁልፍ ተግባራት ዕቅድ ስምምነት አንዲሁም የአዲሱ አመራር ስትራቴጂክ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
አሁን ላይ የዩኒቨርሲቲው ተ /ፕሬዝደንት ዶ/ር ኢ/ር አብደላ ከማል ለውይይቱ ተሳታፊዎች ከላይ በተጠቀሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ እያቀረቡ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በከፍተኛ አመራሮቹ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት