የጠበቃ አስረስ ቃለ መጠይቅ
አርበኛ አስረስ ማረ ከድል በኋላ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያካተተ ስርዓተ መንግስት የመመስረት እቅድ እንዳላቸው ገለጸ
እኛ ካሸነፍን በኋላ ኢትዮጵያ የሚኖራት ህገመንግስት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳተፍ ይሆናል ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ከጎርጎራ ቲቪ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል፡፡
አርበኛ አስረስ የግሌ ያለውን አስተያየት በሰጠበት በዚህ ቃለ መጠይቅ “መነሻችሁ የት ነው ፣ መድረሻችሁ የት ነው” በሚለው ጉዳይ ላይ በሰጠው ምላሽ “እኛ የምናደርገው የፖለቲካ ትግል ነው ፣ መነሻና መድረሻ የሚለው ሃሳብ ርዕዮተ አለም ፣ አሊያም ማኒፌስቶ ያልሆነ ነገር ነው” ብሏል፡፡
ስለዚህ መነጋገር ያለብን ስለትግል ርዕዮተ አለማችን ነው ብሏል፡፡ በዚህም የትግል ርዕዮተ አለማችን የአማራ ብሄርተኝነት ነው ሲል ገልጿል፡፡
አላማችን ደግሞ የብልጽግናውን አገዛዝ ጥሎ በሁሉም ኢትዮጵያዊ የተመሰረተ ስርዓተ መንግስት ማምጣት ነው በሚል አብራርቷል፡፡ የግድ መነሻና መድረሻችሁ ምንድን ነው ከተባለ ግን የአማራ ህዝብ ህልውና ነው ብሏል፡፡
እኛ በብቸኝነት ስላሸነፍን ብቻ የምናረቀው ህገመንግስት አሊያም የምናወጣው ህግ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ብለን ስለማናምን ከድል በኋላ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ፍላጎቶች የታከሉበት ህገመንግስት ይኖረናል ብሏል፡፡
“እኔ እየታገልኩ ያለሁትና አመራር የሆንኩበት ድርጅትም የሚታገለው ለአማራ ህዝብ ነው ፣ ስለዚህ እኛ ያወጣነው ህግ ሌላውንም ይግዛ የሚል እምነት የለንም” ሲል ገልጿል፡፡