በስልጤ ዞን በሚገኙ 45 ትምህርትቤቶች የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠት ሊጀመር ነው
በስልጤ ዞን በሚገኙ 45 ትምህርት ቤቶች ላይ የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠር ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታዉቋል።
የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላ አወል ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት በዞኑ ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል በ45 ትምህርት ቤቶች የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል።በአሁኑ ወቅት ከ1 እስከ 3ኛ ክፍል ማስተማሪያ መጽሃፍት ዝግጅት ተጠናቋል ያሉት ሀላፊው ለማስተማር ለተመለመሉ መምህራን የመማሪያ መፅሀፍ ትውውቅ ስልጠና መስጠቱን ገልጸዋል፡፡
የአረብኛ ቋንቋን ለማስተማር ለተመለመሉ መምህራን ስልጠናው በሚገባ መሰጠቱን መምሪያው ጨምሮ ገልጿል፡፡ተማሪዎች ከእንግሊዝኛ ቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች የውጭ ሀገራር ቋንቋ ትምህርቶችን ቢማሩ ከራሳቸው አልፎ ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉም አቶ ሹክራላ አብራርተዋል።
አቶ ሹክራላ አክለውም ከአረቡ ሀገራት እየተስፋፋ ካለዉ ሰፊ የስራ ዕድል ተጠቃሚነት አንፃር አረብኛን ቋንቋ ከታች ጀምሮ ተማሪዎች ቢማሩ ተመራጭ ነዉ ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።
እንዲሁም ኢትዮጵያ ከአጎራባች ሀገራት ጋር በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር ታለምታደርገዉ የጋራ ጥቅምን መሰረት ያደረገ መልካም ግንኙነት ለመመስረት አጋዥና መሰረት ሊሆን ስለሚችል የአረብኛ ቋንቋ ተማሪዎች መማር ፈይዳዉ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news