የመምህራን ምገባ መርኃ ግብር ዓላማ በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ ማምጣት ነው - ሸገር ከተማ
የመምህራን ምገባ መርኃ ግብር ዋና ዓላማ በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ ማምጣት ነው ሲል የሸገር ከተማ አስተዳደር ገለጸ።
የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍረኪያ ካሳሁን ለፋና ዲጂታል እንዳሉት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት የተለያዩ መርኃ ግብሮች በመተግበር ላይ ይገኛሉ።
ከመርሐ-ግብሮቹ መካከል የተማሪና መምህራን ምገባ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በከተማው በሚገኙ 268 ትምህርት ቤቶች ከ151 ሺሕ በላይ ተማሪዎች በምገባ መርኃ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከቡኡራ ቦሩ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 5 ሺሕ 287 መምህራን ምግብ እየቀረበ ነው ብለዋል።
መርኃ ግብሩ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመንግስት የተወሰደ አዲስ እርምጃ ነው በማለት ገልጸው የመርኃ ግብሩ ዋና ዓላማ በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ ማምጣት ነው ብለዋል።
ከመምህራን ጥቅማጥቅም ጋር ተያያዥነት የሌለው መሆኑንም አስገንዝበዋል።
መምህራን የምገባ መርኃ ግብሩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት የምግብ አቅርቦቱ ለትምህርት የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ ያስቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱን በተረጋጋ መንፈስ ለማከናወን እንዳስቻላቸው ጠቅሰው የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ ትልቅ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ ሊጠናከርና ሊስፋፋ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
#FBC
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news