ንድፈሐሳብን ከተግባር ስልጠና ያጣመረ የወርክሾፕ አደረጃጀት ጥራት ላለው ስልጠና።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የስልጠና ክፍሎችን ለንድፈሐሳብ እና ለተግባር ስልጠና እንዲመቹ አድርጎ በማጣመር እያደራጀ ይገኛል።
ይህ አደረጃጀት ሠልጣኞች ሁለቱንም የስልጠና አሰጣጦች በአንድ ቦታ እንዲሰለጥኑ በማድረግ ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን በሁሉም ስልጠና ክፍሎች ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
የአገራችን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት 70 በመቶ የተግባር ስልጠና አቅጣጫ የተቀመጠ መሆኑ ይታወቃል። ይህንንም ለማሳካት የኢንደስትሪውን ትስስር የሚጠይቅ ሲሆን ስልጠና ተቋማትም ወርክሾፖቻቸውን ይህንኑ የንድፈሐሳብ እና የተግባር ስልጠና ባስተሳሰረ መልኩ ማደራጀት ይገባቸዋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news