እስከ ኒቃባቸው ወደ ትምህርት እንዲመለሱ
በኒቃባቸው ምክንያት ከትምህርት እንዲገለሉ የተደረጉ ተማሪዎች በፊት ሲማሩበት በነበረው አለባበሳቸው ወደ ት/ት እንዲመለሱ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ከስምምነት መደረሱ ተገለፀ!
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በዩኒቨርሲቲው በኒቃባቸው ምክንያት ከትምህርት ከምግብ እና ከመጠለያ እንዲገለሉ የተደረጉ ተማሪዎች እስከ ኒቃባቸው ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለሀሩን ሚድያ ተናግረዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ላለፉት ወራት ሲደረግ የነበረውን መገፋት እና ጭቆና በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ዘንድ ሲታገል እንደነበር አሳውቋል::
በተደረገው ሰላማዊ ትግል እና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት በዛሬው እለት ላለፉት 10 ቀናት ከምግብ ከመጠለያ እና ከትምህርት በኒቃባቸው ምክንያት እንዲርቁ የተደረጉ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ ዘንድ ከስምምነት እንደተደረሰ አሳውቋል::
ይህ ይመጣ ዘንድ ለመብታቸው የታገሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና መላው ለሰብዓዊ መብት መከበር ትብብራቸውን ያሳዩ አካላትን በሙሉ አመስግኖም በዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ለደረሰውና ለሚደርሱ የመብት ጥሰቶች ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን በማድረግ ረገድ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ህብረቱ ለሀሩን ሚድያ አስታውቋል።
በኒቃብ እና በሂጃብ ምክንያት በየጊዜው ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ በደሎች የሚመለከተው አካል በተለይም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ እንዲያገኙ እንዲሰራም ህብረቱ ጠይቋል።
©️ሀሩን ሚድያ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news