የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ ይገባል
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ለሚገኙ የለውጥ ሥራዎች ድጋፍ እንደሚደረግም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሣ በበኩላቸው ፤ ዩኒቨርሲቲው ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመጥን በቂ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news