በጎንደር ዩኒቨርሰቲ የተጠኑ 14 የጥናት ውጤቶች ይፋ ሆኑ
********
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጎንደር ከተማን ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ ጥናታዊ ምርምር ለመፍታት፣ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ከሌሎች የከተማው አመራሮች ጋር በጋራ በመምከር በ2016 ዓ.ም አስራ አራት ዋና ዋና ችግሮችን በመለየት ብሎም ለተለዩት ችግሮች መፍትሄ ለማፈላለግ የጥናትና ምርምር ቡድን በማዋቀር ወደ ስራ ገብቶ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው የጥናት ቡድን የደረሰበትን ውጤት ለሚመለከታቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር አካላት ጥር 28/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አሉምንየም ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይፋ አድርጓል፡፡ የጥናቶቹን ውጤትና ምክረ ሀሳቦች መሰረት በማድረግም ዩኒቨርሲቲውና ከተማ አስተዳደሩ የድርሻቸውን እንዲወስዱ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዕለቱ መርሀ ግብር የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ፣ የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዳይሬክተሮችና ዲኖች፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ኮሚቴ አባላት፤ እንዲሁም የዩኒቨርሰቲው የምርምርና የጥናት ቡድን አባላት ተሳትፈዋል፡፡
ጎንደር ከተማ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ተነጣጥሎ ሊታይ የማይችል ሁለንተናዊ ትስስር በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የገለጹት ዶ/ር አስራት፣ ዩኒቨርሲቲው ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ያደረገውን አንኳር አስተዋጽኦ አውስተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ለጎንደር ዩኒቨርሰቲ ያደረገውን አበርክቶ ገልጸዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ የ 100 ዓመታት አገልግሎቶችን ከመስጠት ጀምሮ በትምህርት፣ በግብርና፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለጎንደር ከተማ ያደረገውን አብይ አስተዋጽኦ በምሳሌ በማስደገፍ ዶ/ር አስራት አብራርተዋል፡፡ የጎንደር ከተማ አርሶአደሮች የእርሻ መሬት እርስታቸውን በነጻ በማስረከብ ያሳዩት ጌዜ የማይሽረው አስተዋጽኦ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ የሰጠው ማስፋፊያ ቦታና ለንጹህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚያደርገው ተባባሪነት፣ ጎንደር ከተማ- ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ካደረገው አስተዋጽኦ መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
ከጎንደር ዩኒቨርሰቲ ጋር በሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ላይ በአብሮነት በመስራታቻው ኩራት እንደሚሰማቸው በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ ናቸው፡፡ ም/ከንቲባዋ በሁሉም ዘርፍ በበቂ ሁኔታ የተማረ የሰው ኃይል ካለ ብሄራዊ ጥቅምን ያለምንም ችግር ማስከበር እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ መሰረት በጎንደር ከተማ ተግባራዊ የሚደረጉት 14ቱ የጥናት ውጤቶች ይዘት እና የደረሱበትን ደረጃ የገለጹት የጎንደር ዩኒቨርሰቲ የምርምር እና ቴክኖሎጅ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕ/ር ቢኒያም ጫቅሉ፣ የጎንደር ከተማና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያላቸው መልካም ግንኙነት ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ወጣትና አንጋፋ መምህራንና ተመራማሪዎች በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸው እየጨመረ መምጣቱንም አያይዘው ተናግረዋል፡፡
በትምህርቱ ዘርፍ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤታማ ማድረግ፣ የጤና ተቋማትንና አገልግሎትን ማዘመን፣ ቱሪዝምን፣ የንግድ ስርዓቱንና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣ ማዘመንና ማሳደግ፣ በግብርናና በከተማ ውበት-ከተማዋን ማልማትና ማስዋብ፣ ከተማዋን ማሳደግ፣ ስራ ፈጠራን በተመለከተ፣ ሲቪል ሰርቪስን በተመለከተ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር እንዲሁም ሰለምና አስተዳደርን የተመለከቱ አብይ ርዕስ ጉዳዬች በጎንደር ከተማ ከተዳሰሱት ጥናቶች ምካከል እንደሚጠቀሱ ከፕ/ር ቢንያም ጫቅሉ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በመጨረሻም በዶ/ር አስራትና በወ/ሮ ደብሬ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመጪው አምስትና ስድስት ቀናት ውስጥ በየሴክተር መስሪያ ቤቶች ውይይት ተደርጎ ለአጠቃላይ ውይይት ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ የፖሊሲ መግለጫ (Policy Brief) ርክክብ በማድረግ የዕለቱ መርሀ-ግብር ተጠናቋል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news