የአስገድዶ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው መምህር በእስራት ተቀጣ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ለፎ ወረዳ ኦሎኮሊ 02 ቀበሌ ውስጥ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል በተከሰሰው መምህር ላይ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተገለፀ::
ከምዕራብ ሸዋ ዞን ፓሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ተከሳሽ መዝገቡ አበራ የተባለው መምህር ግንቦት 21 ቀን 2016ዓ.ም በኤጀሬ ለፋ ወረዳ ኦሎንኮሚ 02ቀበሌ ውስጥ በመምህርነት ሙያ እያገለገለ እያለ የአስራ ስድስት ዓመቷ ታዳጊ ላይ የመድፈር ጥቃት ፈፅሟል::
ተከሳሹ መምህር የአስራ ስድስት ዓመቷን ታዳጊ እናት በሰራተኝነት በማስጠጋት እናት እና ልጇን በቤቱ በማስጠጋት እያኖራቸው እያለ ግንቦት 21ቀን 2016 ዓ.ም የመምህሩ ህጋዊ ሚስት የእርግዝና ክትትል ለማድረግ ወደ ሆስፒታል በምትሄድበት ጊዜ ብቻዋን እንዳትሆን የታዳጊዋ እናት አብራት መሄዷ ተገልጿል::
ተከሳሹም የታዳጊዋ እናት ከባለቤቱ ጋር ተከትላ መሄዷን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በቤት ውስጥ ብቻዋን በማግኘቱ የመደፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተረጋግጧል:: የደረሰባትን የአስገድዶ የመደፈር ጥቃት ለወላጅ እናትዋ እና ለመምህሩ ባለቤት ከሆስፒታል ሲመለሱ በማሳወቋ ወዲያውኑ ጉዳዩን ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው በቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስም የመደፈር ጥቃት የደረሰባትን ታዳጊ ሆስፒታል በመላክ በማስመርመር እና የምርመራ ውጤቱን በመቀበል የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለአቃቢ ህግ ልኳል።አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሹ ላይ ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን በውሳኔው ቅር የተሰኘው የተበዳይ ቤተሰብ እና አቃቤ ህግ ጉዳዩን በይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማቅረባቸው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎትም የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ በመሻር በተከሳሹ ላይ በ ዘጠኝ አመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news