ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ በይፋ አስጀምረናል- አቶ አረጋ ከበደ
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አካል የሆነውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ በይፋ አስጀምረናል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አስታወቁ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፤ ዛሬ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማስፈጸሚያ ዕቅድን ከአሥተዳደር ምክር ቤት አባላት ጋር ገምግመናል ብለዋል።
የሪፎርም ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን አረጋግጠናል ያሉት አቶ አረጋ፤ የሪፎሩሙ አካል የሆነውን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራም በይፋ አስጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ለሕዝባችን ዘላቂ ልማት እና ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት የሪፎርም ሥራውን ከፍ ባለ ቁርጠኝነት ለመፈፀም እንሠራለን ብለዋል፡፡
#FMC
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news