ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አዋጭ ፋውንዴሽን በወረዳ 06 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 66 የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 5 ቄብ ዶሮ ድጋፍ አድርጓል።የዚህ ድጋፍ ዋነኛ ዓላማ ህብረተሰቡ ባለው ውስን ቦታ በዶሮ እርባታ ራሱን በመቻል የቤተሰብ ፍጆታ እንዲሸፍን ለማስቻል እንዲሁም በቀጣይ የተሻለ ስራ ሰርተው ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች መትረፍ እንዲችሉ ነው ሲሉ የአዋጭ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብይ በሻህ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 እና 08 እንዲሁም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ ለሆኑ ለ172 በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርቷል።