11ኛው ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሸን፣ባዛርና ሲምፖዚየም ተጠናቀቀ።
ከጥር 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲካሄድ የነበረው 11ኛው አገር አቀፍ ኤግዚቢሽን ፣ባዛርና ሲምፖዚየም በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በመዝጊያ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
የኩነቱን መጠናቀቅ ተከትሎ በተላለፈው መልዕክ ባለፉት 5ቀናት በተካሄደው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የተመረቱ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማህበረሰብ በማቅረብ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱ ተገልፃል።
በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ ከ350 በላይ የሚሆኑ የኅብረት ስራ ማህበራት እና ሌሎች ድርጅቶች ተሳታፊ እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የገበያ ትስስር መፍጠር የተቻለበት እንደነበር በመድረኩ ለይ ተነስቷል።
ለ2017ዓ.ም ኤግዚቢሽን ባዛርና ሲምፖዚየም ተሳታፊዎች እና በየደረጃው ስፖንሰር ላደረጉ ተቋማት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።