አዋጭ በፋውንዴሽኑ በኩል ለዲቦራ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም አዋጭ ፋውንዴሽን በዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ቢሮ በመገኘት የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በድጋፉ ወቅት የአዋጭ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ መልእክት ሲያስተላልፉ አዋጭ በአዋጭ ፋውንዴሽን በኩል ገንዘብ ነክ ያልሆነ ዘላቂ ድጋፎችንም በማድረግ ሁለቱ ፋውንዴሽኖች በአጋርነት መስራት የሚያስችላቸውን ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል፡፡
የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው አዋጭ ያደረገላቸውን ድጋፍ በማመስገን አዋጭ ሁሌም ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጎን እንደሆነና በተለያየ መንገድ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑንም መስክረዋል፡፡ በድጋፉም ላይ የአዋጭ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ ተገኝታ መልዕክት አስተላልፋለች።