……የቀጠለ
ይህ አረመኔ ሥርዓት በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ የሚገኘውን የጦርወንጀል ለማድበስበስና የሥልጣን ፍትወቱን ለማጽናት ምናልባትምሥርዓተ መንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ የሚጓዝባቸው መንገዶችደመ ነፍሳዊ፣ አላዋቂ፣ ሕገ ወጥ፣ መርኅ አልባ፣ ከምንም በላይ ሀገርንየመምራት ሞራል፣ ክህሎትና እውቀት የሌለው ፍጹም አቅመ ቢስ መሆኑን ያረጋግጣል። ብልጽግናን መታደግ የሞተን ሰው ከመቃብር እንደ ማስነሳት ነው፤ ብልጽግናን እንደ መንግሥት ማስቀጠል የጸሐይን መውጫ በምዕራብ እንደመጠበቅ ነው፤ የብልጽግናን የሥነ መንግሥት ውቅር መሠረታዊ እሳቤዎችን ማስቀጠል በአማራሕዝብ ላይ የሚፈጸምን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደ ማስቀጠል ብሎም የጦር ወንጀሉም ተባባሪነት ነው፤ ብልጽግናን በገሐድ ማስቀጠል አይደለም ሥርዓቱ እንዲቀጥል በንግግርና በሀልዮም ጭምር መደገፍ ታሪክ ይቅር የማይለው አማራ እንደሕዝብየሚጠፋበትን ጦርና ጎራዴ እንደማቀበል ነው።
ስለሆነም ሥርዓቱን ከነእኩይ አስተሳሰቡ ለማስወገድ የሚደረገውን የአማራ ሕዝብየኅልውና ትግልን ለማኮላሸትና ለመጎተት የሚታትሩ ከብልጽግናው መዋቅር ሹማምንት እስከ የሃይማኖት አባትነትና የሽምግልና ጭምብል አጥላቂዎች፣ የአማራን ሕዝብ በምጣኔ ሃብት እያደቀቀ ለሚገኝ ሥርዓት በፋይናንስ ደጋፊ ባለሃብቶች እስከ ሳይበሩ ዓለም የተኮለኮሉ እኩይ የሥርዓቱ ሎሌዎች መኖራቸውን በውል እናውቃለን።
የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ አደረጃጀቶችበሚከተሉት ጊዜ የማይሰጡ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን አቋም፣ አቅጣጫና ማስጠንቀቂያዎችንም ጭምር ለሕዝባችንና ለሠራዊታችን ከምንም በላይ ላላዋቂ የሥርዓቱ ዘቦች መግለጽ እንወዳለን። በዚህ መሠረት፦
1ኛ. ሽምግልና ትርጉሙ፣ አፈጻጸሙ፣ ተሳታፊዎቹ፣ ተጠቃሚዎቹና መሰል ዝርዝር ጉዳዮችን በወጉ ስንመረምር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሐቀኛ የፍትሕ ተቋም ነው። እንዲህ ያለ ሐቀኛ ተቋም ደግሞ መርሁፍትሕን በሐቅ ምርኩዝነት መዳኘት ዘወትራዊ ግብሩ ነው። በሽምግልና በዳይን ይገስጹበታል፤ ነውረኛን ያርሙበታል፤ ገዳይን ይቀጡበታል፤ ሸረኛን ቀጥቅጠው ያስተካክሉበታል፤ ሐገርን ሕዝብን ግለሰብንም ጭምር የበደሉ አካላት ያለአንዳች ማኅበራዊ ደረጃ እኩል በሐቅ ይበየንባቸዋል። የተበደሉ አካላትም ይካሳሉ፤ ፍትሕን በልኩ ያገኛሉ። ቅሉ የሽምግልና ወጉ ይህ ሆኖ እያለ ሐቀኛውን ነባር የፍትሕ ተቋም ለሆድ፣ ለጥቅም ማዋል፣ በዳይም ተበዳይም በዓለም አደባባይ እየታወቀ የአይሁድ ሸንጎ አስፈጻሚ የሃይማኖት አባትነትን ጭምብል ያጠለቃችሁ፣ የፍትሕን ምንነት የማታውቁ ነገር ግን በቁሳዊ ሃብታችሁ የታወቃችሁና በልዩ ልዩ ጉዳዮች እውቅናን ያገኛችሁ አካላት በቅንጅት የጦር ወንጀለኛውን በርባን አብይ አሕመድን ነጻ እንዲሆን ሽታችሁ እንደ ክርስቶስ ያለበደሉ መስቀል ላይ የተቸነከረውን አማራውን የማስጨረስ ፕሮጀክቱ ተባባሪ ሆናችሁበማግኘታችን እጅጉን አፍረንባችኋል፤ አዝነንባችኋልም።
በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው መንግሥት መር የዘር ማጥፋት ድርጊት ከሽምግልና የተሻገረ፣ ሥርዓታዊ ሥር ነቀል ለውጥን የሚሻ፣ ወንጀለኞችም በዓለም አቀፍ የጦር ወንጀልና በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ ስላልሆነ ከወንጀለኛ ጋር የዘረጋችሁትን ተባባሪነት እግራችሁንም እምሯችሁንም እንድትሰበስቡ እየመከርን በየቀኑ የሚገደለው ሰው መሆኑንም ተገንዝባችሁ ለእውነትና ለፍትሕ ያላችሁን ውግንና ጨፍጫፊውን ሥርዓት በአደባባይ በማውገዝ እንድታሳዩንም እንጠይቃለን።
2ኛ. የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል በሥርዓቱ ወራሪ ሠራዊት ላይየውጊያ የበላይነትን ሙሉ ለሙሉ ከመውሰዱ ባሻገር ምድር ላይ ያሉሐቀኛ ሁነቶችን በመግለጥ የሚዲያና የፕሮፓጋንዳ የበላይነት ተወስዶበት መንፈራገጥ ላይ ይገኛል። የተወሰደበትን የሚዲያ የበላይነት ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተለያዩ ቀናት የተነገሩትንየድምጽ ቅጅዎች በማገጣጠም የኅልውና ታጋዩን መስተጋብር አበላሻለሁ የሚለው አስተሳሰብና ድርጊትም የሥርዓቱን አላዋቂነት ከመግለጡ ውጭ ከቶ ምንም ሊባል አይችልም። እንደዚህ ያለው የሳይበሩ ዓለም ተግባርም ቀድመን ያወቅነው፣ ድሮን፣ ታንክና ሞርተር ያልበገረው ሠራዊታችንም በወጉ የሚገነዘበው የጠላት እቅድና ፍላጎት መሆኑን እያስገነዘብን፣ አንዳንድ አመራሮቻችን ላይ የሚደረጉ ፍረጃዎቸም የዚህ ፕሮጀክታቸው አካል መሆኑን መግለጥ እንወዳለን።
3ኛ. በመጨረሻም የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ብዙ ነገራችንን ያጣንበት በአንጻሩ የብልጽግናን መዋቅር በአጭር ጊዜያፈራረስንበት፣ ሕዝባችንን አስተባብረን በአሸናፊነት መንገድእየተጓዝን የምንገኝበት ግዙፍ አብዮት ነው። እንዲህ ያለውን ሕዝባዊ አብዮት የሚጎትት፣ የሚያቀጭጭ፣ የሚያኮላሽ ምድራዊ አደረጃጀትና መዋቅሮችም ፈርሰዋል። ስለዚህ የማይድን ሥርዓት ውስጥ የምትገኙ የሚሊሻ፣ የአድማ ብተና እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት እስከ ጥር 15/2017 ዓ.ም ድረስ በየቀጠናው ለሚገኘው የፋኖ አደረጃጀት በሠላማዊ መንገድ እጃችሁን እየሰጣችሁ፣ የተሃድሶ ሥልጠናዎችን እየወሰዳችሁ ሥምሪት ተቀብላችሁ ትግላችንን ወደፊት እንድናስፈነጥረው የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።
ኅልውናችን በተባበረ አንድነታችን!!!
አርበኛ ሐብቴ ወልዴ.............የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ዋና አዛዥ
አርበኛ ባዬ ቀናው................የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ