ክርስትና እና የመደመሩ ባለ ራዕይ ብልጽግና!
---●----
ከበርናባስ በቀለ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ወደ ምድር የመጣው በሮም ዘመነ መንግሥት መኾኑ ይታወቃል። እርሱ የመጣው ታዲያ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስርዓት (አስተዳደር) ሊመሠርት እንጂ ለዓለም መንግሥት ጥገናዊ ለውጥ ሊያደርግ አልነበረምና የመንግሥቱን አሠራር መርኾዎች በሮም መንግሥት ለማጋባትና ለማስረጽ ሲጥር አይታይም።
እንኳን ከሮም መንግሥት መሲሓዊውን ንጉሥ (the Messianic king) ሲጠብቁ ከኖሩ ከይሁድነት እምነት መሪዎችና ማኅበረሰብ ጋር አብሮ ለመሥራት ሲፈራረም አላነበብንም። የሮም መንግሥት በጊዜው ኃያልና ገናና ከመኾኑ የተነሳ ከርሱ የሚበልጥ አንድ ሉዓላዊ መንግሥት እንዳለ ሲነገረው እንኳን ሊሰማ የመንግሥቱን ዜና አብሳሪዎች ሊያርድ ተያያዘ።
የእግዚአብሔር መንግሥት ሕጋዊ ወኪል፣ ሰባኪና ንጉሥ ኾኖ የመጣው ጌታችን ኢየሱስ ለሮም መንግሥት የደህንነት ስጋት (threat) እንጂ ተፎካካሪ ፓርቲም ኾነ የፖለቲካው ሹመኛ ሊኾን አይችልም። መንግሥቱ ከዚህ ዓለም እንዳይደለች ሲሰብክ የመጣው ይህ ንጉሥ የሚያስተዋውቀው አስተዳደር በዓይነቱ ለየት ያለ ከመኾኑም አልፎ የሮምን መንግሥት ፍልስፍና አፈር ከድሜ የሚያበላ ነበር።
ስለዚህ ሮም ይህን ሰው ሊሸልመውና የልማት አጋሩ አድርጎ ሊሾመው አይችልም። የወንጌላትን ትረካ በቅጡ ያነበበ ሰው ጌታችን ኢየሱስ እና የሮም መንግሥት ሆድና ጀርባ እንጂ እጅና ጓንት ኾነው ስለመኖራቸው ሊያስብ አይችልም። መዝሙረኛው በቅኔው ዳንኤልም በትንቢቱ የጻፉላት ሁሉን የምትገዛዋ የእግዚአብሔር መንግሥት የሮምንም አስተዳደር በክንዷ ፈጭታ በሁሉ ላይ ኃያል መኾኗ እንዲገለጥ የመጣው ኢየሱስ እንዴት ከሮም ባለ ሥልጣናት ጋር የስምምነት ውል ሊፈራረም ይችላል? አይኾንማ።
"የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ የመጣው መሲሕ በምን ሂሳብ "የመንግሥትነት ልኩ እኔ ነኝ" ከሚል የሮም መንግሥት ስርዓት ጋር ቡና ሊጠራራ ይችላል? ጽድቅንና ፍርድን የዙፋኑ መሠረት ያደረገው የልዑሉ እግዚአብሔር መልእክተኛ ዙፋኑን በግፍ ካጸናው የሮም መንግሥት ጋር እንዴት አሻሼ ገዳሜ ሊል ይችላል? በፍጹም ሊኾን አይችልም።
እንኳን ጌታችን ኢየሱስና ሮም የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ቡድንና ሮም መንገዳቸው ለየቅል ነው። የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ዳዊታዊውን ንጉሥ (Davidic king) የሚጠብቁ የሩቅ አገር ተጓዦች ናቸው። በጊዜው በዙፋኑ ላይ የነበረው ንጉሥ ለእነርሱ የመጨረሻ (ultimate) ንጉሥ እንደኾነ የማያምኑና በሁሉ ላይ ሊያይል የሚመጣውን የአምላካቸውን መንግሥት እየተጠባበቁ በተስፋ የሚያድሩ ናቸውና (ግን ምን ያደርጋል! ከመንግሥቱ ጌታ ጋር ተላልፈዋል)።
እንኳን የሮም መንግሥት የይሁድነት እምነት ተከታዮችና ኢየሱስ ተግባብተው አያውቁም። የይሁድነት ሃይማኖት በሮም መንግሥት ሕጋዊ ፈቃድ (ሽፋን) ያለው ተቋም ቢኾንም ግን በምኩራቦቻቸው አምላካቸውን እያመለኩ የሚመጣውን ንጉሥ ይጠባበቁ ነበር። ችግሩ እነርሱ የመሲሑን መንግሥት የሚጠብቁት ካሉበት ፖለቲካዊ ጫና ነጻ እንዲያወጣቸው እንጂ በኃጥአት እስራት ነጻ ስለ መውጣታቸው አይደለም።
ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ኃጥአት በአመጸኞች እጅ ወድቆ የመስቀል ሞት የተፈረደበት በሮም መንግሥትና በእነዚሁ የአይሁድ ሃይማኖት እንቅስቃሴ አራማጆች ጥምረት ነበር። ጌታችን መከራ የተቀበለው በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን የመኾኑን መቼስ አታጡትም። ብቻ ምን አለፋችሁ፦ የሮም መንግሥት ኢየሱስን ሲሰቅለው እንጂ ሲሸልመው አልተመለከትንም፤ ሲፈርድበትና ሲያሳድደው እንጂ ወንበሩን ሲለቅለት አላየንም።
ከጌታችን ኢየሱስ ሞት በኋላ ይኸው መንግሥት ተከታዮቹን ማሳደዱን ተያያዘ። "የዚያ ሰው መንገድ መጥፋት አለበት" ብሎ ቀንና ለሊት ይሠራ እንደነበር የምናውቀው የሮም መንግሥት ለመሲሑ መንገድ ተከታዮችም የሚበጅ አልኾነም። የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አማኞች ብዙ እንግልትና መከራ ይደርስባቸው እንደነበር የአዲስ ኪዳን ጽሑፎች በግልጥ ይነግሩናል።
ሮምና የመሲሑ መንግሥት ተከታዮች (ደቀ መዛሙርቱ) እጅና ጓንት የኾኑበትን ዘመን አላየንም። እውነተኞቹ የክርስቶስ ተከታዮች እንኳን ከሮምና ከይሁድነት ከእናት ከአባቶቻቸው ተለይተው ለመሲሑ መንገድ ራሳቸውን የሰጡ ናቸውና ከሮም መንግሥት የጋራ የምክክር መድረክ የሚባል ነገር አይታሰብም።
ሮም "አገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ልማት" የሚባል ኮሚሽን አቋቁማለኹ ብሎ ቢያስብ ከደቀ መዛሙርቱ ለካቢኔነት ቢመለመል "የከፍታ ዘመን" ብሎ የሚያስብ አንድም ደቀ መዝሙር የለም። ሲጀመር ሮም ራሱ ሊገድላቸው እንጂ በመንግሥቱ ሊሾማቸው መቼ ይፈልግና! የይሁድነት አቀንቃኞችና የሮም መንግሥት መሲሑን ተባብረው እንደሰቀሉት ሁሉ ክርስቲያኖችንም ተባብረው ያሳድዱ ነበር።
እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለሮምም ለይሁድነትም ግራ ነው። በቃ አይገጥምም። የመሲሑ መንገድ ተከታይ ነውና መከራ፣ ስደትና ሞት የሕይወት ዘዬው ነው። የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አማኞች ታዲያ መከራው በርትቶባቸው ነበር። መፈናፈን እንዳይችሉ ከወዲህ የሮም መንግሥት ከወዲያ ደግሞ የይሁድነት አቀንቃኞች ናላቸውን ሲያዞሩ እምነታቸው ጫና ውስጥ ሲወድቅ ከመልእክታት አንብበናል።
ከአዲስ ኪዳን ጸሐፍት ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ፣ ይሁዳ፣ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊና ሌሎችም ጸሐፍት በመከራ ውስጥ የሚያልፉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ የሚመክሯቸው "እግዚአብሔር የሮምን መንግሥት አሳልፎ ይሰጣችኋል! ባለ ሥልጣናት ከእናንተ መካከል ይመለመላሉ" እያሉ አልነበረም። ይልቅ ያነበብነው "የመንገዱ ባሕርይ ነው! የሚሞተው ስጋችሁ በጌታ ቀን ሕይወትን ያገኛልና ሞትን አትፍሩ፤ ዘመኑ በጣም ትንሽ ነውና ጽኑ" ሲሉ ነው።
አንዳንድ አማኞች መከራው እጅጉን ስለ ከበዳቸው ወደ ቀድሞ ሃይማኖታቸው (ይሁድነት) ሊመለሱ አስበው ነበር። የዕብራውያን ጸሐፊ "ማፈግፈግ" (drifting away) ብሎ የሚጠራው ይህንኑን (ዕብ 2:1) ሲኾን ጴጥሮስ ደግሞ "ቢያሰፈልግ አሁን (ለጥቂት ጊዜ) በልዩ ልዩ መከራ አልፋችኋል... ግን በኋላ ክርስቶስ ሲገለጥ እጅግ ደስ ይላችኋል" (1ጴጥ 1:6-7) ይላል። የጌታ ወንድም ያዕቆብ ደግሞ እምነታችሁ ተፈትኖ ጽናትን (Perseverance) ያፈራላችሁና ምሉዓንና ፍጹማት ትኾናላችሁ (መከራው purify ያደርጋችኋል) እያለ የመከራቸውን ዓላማ redifine ያደርጋል (ያዕ 1:4)።
ቆይ ግን፦ አማኞቹ ወደ ይሁድነት የሚመለሱት ለምን ይኾን? ይሁድነት በሮም የሚታወቅ (ጫናው ስር ያለ) ሃይማኖት ስለኾነ ነዋ! ሮም ይሁድነትን በጫናው ስር አድርጎ ለመንግሥቱ አሠራር በሚመች በልኩ ይዞታልና ለዙፋኑ ስጋት አይኾንበትም፤ ክርስቶስ ግን አካኼዱ ለያዥ ለገናዥ እንደማይመች ያስተዋለው ሮም ሰቅሎት ተገላግሏል። ይሁድነት ሮም ከሚያወጣው አዋጅ ስር ስለኾነ ስጋቱ አይደለም፤ ስለዚህ ሮም መከራ አያደርስበትም። የመጀመሪያዎቹ አማኞች ከመከራው ለማምለጥ በገዢው መንግሥት በአዋጅ ወደተመዘገበው (officially registered ወደኾነው) የይሁድነት ሃይማኖት መመለስ ነበረባቸው።