የመሲሑ ተከታዮች officially እንደሚሰደዱ እንጂ register እንደሚደረጉ ከመሪያቸው የተሰጣቸው ተስፋ የለምና ያላቸው አማራጭ በመከራው እስከ መጨረሻ መጽናት ነው። ሲያልፍም የተሰጣቸው ትልቅ ተስፋ የአምላካቸው የእግዚአብሔር መንግሥት ንጉሥ ዳግመኛ መመስ ነው። መከራቸው officially የሚያበቃው ያኔ ነውና እስከዚያው officially ይሰደዳሉ፣ ይወገዛሉ፣ ይሞታሉም።
የአዲስ ኪዳን ጸሐፍት የሚነግሩን በጊዜው ዙፋን ለተቆናጠጡ ገዢዎች በጌታ (having Christ's mind) እንድንታዘዝ እንጂ ከአሠራሩ ጋር ጋብቻ እንድንፈጽም አይደለም። በእኛ ዘመን ጭራሽ የሮም መንግሥት ተሿሚዎች፣ የፍልስፍናው አሳላጮችና ካቢኔዎቹም እኛው ነን። የሮምን መንግሥትና ክርስቶስን ያፋቀርንና አብሮ ሠራተኞች ያደረግን በዓለም ታሪክ ምርጦቹ የእርቅ ኮሚሽን ጀግኖች እኮ ነን!😎
ስለ ዕውቅና ያለን አመለካከት ደግሞ እንዴት ሸውራራ (ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ) እንደኾነ ሳስብ ሃዘኔ ይበዛል። ክርስትና በመንግሥት ዕውቅና የነበረው ከ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ይልቅ በ1ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። ከአሁኑ ብልጽግና ይልቅ በጥንቱ ደርግ ዘመን ነው። እንዴት ማለት ጥሩ አይደል?
ሕጻኑ ኢየሱስ የተወለደ ጊዜ ሄሮድስ ጨቅላ ሕጻናትን ሁሉ ያስጨፈጨፈው ለምን ነበር? እርሱ የአይሁድ ንጉሥ እንደኾነ አውቆ አይደለምን? የሮም መንግሥት መሲሑን የሰቀለው ለምን ነበር? መንግሥቱና አሠራሩ ከእነርሱ የማይገጥም መኾኑን ስላወቀ አይደለምን? የኮሙኒስት እምነቱ (እግዚአብሔር የለሹ) የደርግ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን የሚያሳድደው ለምን ነበር? "እግዚአብሔር አለ" የምትል ወኪል ድምፅ መሆኗን ስላወቀ አይደለምን? የዚህ ዓለም መንግሥት እውነተኛ የመሲሑ መንግሥት ተከታይ መኾንህን ሲረዳ ያሳድድሃል፤ ያኔ አንተ በእነርሱ ዘንድ ታውቀሃል።
መታወቅ የሚባል እውነታ የሚረጋገጠው እግዚአብሔር እኛን በሚያውቀን መንገድ ሰዎች ሲያውቁን ነው። ቅዱሱ መጽሐፍ በነገረን ሕይወትና ማንነት ሰዎች እኛን ሲያውቁን ያኔ በርግጥ ታውቀናል፤ ለመታወቅ ብለን የምናደርገው ነገር አይኖርም እኮ፣ ግን የመሲሑ መንገድ ተከታዮች መኾናችን እንዲያው ይታወቃል።
እኛ መታወቅን ከአደባባዮች ስብሰት፣ ከቤተ እምነቶች ግንባታ፣ ከመቃብር ስፍራዎች፣ ከሚዲያ ሽፋን፣ ከሥልጣን መደብ እኩልነት እናም በመሰል ርካሽ መወደዶች ተክተናል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር እኛን በሚያውቀን መንገድ የታወቅን ይመስላችኋል? ከዚያም ተደራጅተን ስደትንና መከራን የሚከላከል ተቋም መሠረትን ክርስቶስን የሰቀለው የዓለም መንግሥት ለክርስቲያኖች ከለላ እንዲያደርግ ተማጽኖ አቀረብን።
አቤቱ አምላኬ ሆይ፦ አንተ በምታውቀን በዚያ መንገድ ብቻ እንድንታወቅ የርካሽ ዕውቅና ቅጥሮቻችንን አፍርስልን።
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊