ትንሿ ጆሮዬ...
----●----
ከበርናባስ በቀለ
ጆሮዬ ዲሿ (ውጫዊ ክፍሉ) በተፈጥሮ ትንሽዬ ነው። የቅርብ ወዳጆቼ አስተውላችኹ ታውቁ እንደኾነ አላውቅም። "አሁን ይኽ ጆሮ እንዴት ይሰማል? ደግሞ እኮ ልቅም አድርገህ ነው የምትሰማው" ላላችኹኝ ጆሯችን በዋናነት የሚሰማው በውስጥ ክፍሉ እንጂ በውጭው አንቴና እንዳይደለ ያወራሁትንም አልረሳውም።
ሙባረክ ይባላል፤ የምኖርበት ሰፈር ያለ ሕጻን ልጅ ነው። ሰላም ካልኹት በኋላ ጆሮውን ይዤ ይኽ ምንድነው? አልኹት፤ "እንዴ! ጆሮ ነዋ!" አለኝ። "ያንተም ያው!" ብሎ ወደ ጆሮዬ አመለከተኝ ("አንተ የሌለህን ባዕድ ነገር ያገኘኽብኝ መሰለህ?" ይመስላል አባባሉ)።
ከዚያም ጆሮዬን እያየ "ያንተ ግን ትንሽ ነው!" አለኝ። እኔም አዎን ትንሽ ነው። አላሳዝንም? አልኹት። "ምን ኾኖ ነው?" ሲለኝ በቃ የተሰጠኝ ይኽ ነው! ብዬ መለስሁት። ከንግግሬ የጆሮዬ ማነስ ጉዳይ በጣም ያሳሰበኝ እንደኾነ አስቧልና እኔም፦ 'ያንተ በጣም ትለቅ ነው! ታድለህ! ለእኔ ትንሽ አትሰጠኝም? አልኹት። "እንዴት ልስጥህ?" ሲለኝ መቁረጫ አለኝና ከዚህ መልስ ልውሰድ? ስለው "ውሰድ!" ብሎ እርፍ።
ኪሴ አካባቢ ተፍ ተፍ ብዬ ከቁልፍ ማንጠልጠያዬ ስለት ያለውን አንዳች ፈለግሁ። "በዚህ እድሜ ግን ቁልፍ ማንጠልጠል?" ያላችኹኝን አልሰማችኹም። ወደ ልጁ ልመልሳችኹ፦ ስለታም ነገሩን ይዤ ወደ ጆሮው ሳቀርብ ጸጥ! "ውሰድ..." ይለኛል። ፍርሃትና መርበትበት ፊቱ ላይ አይነበብም! ምን አይነት ቅንነት ነው? 😥
በዚህ ጊዜ ብዙ ሰው እንኳን የጆሮውን አካል ቆርጦ ሊሰጥህ ጥቂት ሊሰማህ (ጆሮውን ሊሰጥህ) አይፈቅድም እኮ። ምናለ ይኽ ብላቴና እኛ ወደምንኖርበት የብልጠት ዓለም (Calculative ኾኖ ወደሚኖርበት stage) ባይመጣና በዚሁ ልብ ቢያድድግ ብዬ አስብኹና ይህ የልጅነት ንፁህ ልብ ብቻ እንደኾነ ተረድቼ ስሜው አለፍሁ። ትንሿን ጆሮዬን ሰጥቼ የሰማኹት ልጅ ጆሮውን ቆርጦ ሊሰጠኝ የሚፈቅድ ኾኖ ሳገኝ ጆሮዬን ስለነሳዃቸው ሰዎች ንስሐ እየገባኹ ወደ ጉዞዬ!
ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊