#ፀሎተ ሀሙስ
#ሀሙስ ምሽት ጌታችን ያደረገልን ትህትና ዮሐንስ 13
እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ
እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም
ትላላችሁ።
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ
እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ
ይገባችኋል።
እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ
ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም።
መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። 17 ይህን ብታውቁ
ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
ስለ ሁላችሁ አልናገርም እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ
ነገር ግን መጽሐፍ፦ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን
አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከአሁን ጀምሬ
አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር በመጀመሪያነት ያጋሩት፦
በሰሞነ ህማማት የሚገኙ እለታትና ስያሚያቸው ........እለተ ሀሙስ -በዚህ እለት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ለመግለፅና ለአርያነት ፀሀፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲፀልይ በማደሩ ምክንያት ፀሎተ ሀሙስ በመባል ይታወቃል ፡፡
ትህትና ፍቅር መታዘዝ እንድሁም የአገልግሎትም ትርጉም
ለማስረዳትና ለማስገንዘብ እርሱ ጌታ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ህፅበተ እግር በመባልም እንደሚጠራም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ ፡፡
ሀዋርያው ቅዱስ ዮሀንስም እግራቸውን አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንድህም አላቸው ያደረኩላችሁን
ታስተውላላችሁን እንግድህ ጌታ መምህር ስሆን እግራችሁን
ካጠብሁ እናንተ ደግሞ ለታናናሾቻችሁ እንድሁ ታደርጉ ዘንድ ይገባችኀል ሲል ተናግራል፡፡ ይኸውም ዮሀንስ ወንጌል 13 ፣12
- 20 በዝርዝር ይገኛል ፡፡
ይህ ለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋየ ነው እንካችሁ
ብሉ ይህ ፅዋ ለእናንተ የሚፈሰው የሀዲስ ኪዳን ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ሚስጥረ ቁርባንን የመሰረተበት ወይንም
እራሱ ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሚስጥረ ቁርባንን የጀመረበት እለት በመሆኑ የሚስጥር ቀን በመባል ይጠራል ፡፡
ይኸውም የሰው ልጆች ስጋውንና ደሙን ተቀብለው ከእርሱ ጋራ
አንድነትንና ህብረትን እንድኖረን ጥንተ ጠላት ዳቢሎስን ድል
ነስተን ሰማያዊዩን እርስት እንድንወርስ ሊያደርግ ነው፡፡ ይህም በማቴወስ 26 ፣ 26 - 29 በዝርዝር ይገኛል ፡፡
አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጎት ቀስ ብለው
መጥተው የያዙበት ስለሆነ በዚህ እለት በለ ሆሳስ ወይም ብዙ
የጩኸት ድምፅ ሳይሰማ የቅዳሴ ስርአት ይፈፀማል ፡፡
ስለሆነም መላው ህዝበ ክርስቲያን በዚህ የህፅበተ ሚስጥር የፀሎት እለት በሆነው በዚህ እለት በንስሀ ታጥበው የጌታን ስጋና ደሙን እንድቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅኖት ታስተምራለች ፡፡
እኛም በንስሀ ታጥበን ወደ አምላካችን ቀርበን ስጋወ ደሙን
ልንቀበል ይገባናል የጌታችን ቸርነት ፍቅሩ የእመ አምላክ
የንፅሒተ ንፁሀን የድንግል ማርያም ምልጃ የመላክት ጥበቃ
የሠማአታት ፀጋ በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን
አሜን አሜን !!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/yetewahedofera