Репост из: የተዋሕዶ ፍሬዎች
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
-----------------------------------------------
አንድ ጥያቄ አለኝ!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ጥያቄ ፦
፩ . በስሙነ ሕማማት ማማተብ ፣ ማዕድ መባረክ ፣ መልክዐ መልክ መድገም አይፈቀድምን?
፪ . ሰሙነ ሕማማት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ማማተብ ፣ ማዕድም ሲቀርብ ባርኮ መቁረስና ስለ እነሱ ብሎ ቡራኬ መስጠት የተከለከለ ነው ይባላል፡፡ ትክክል ነውን? ለምን?
፫ . በተጨማሪም መልክዐመልኮች አይደገሙም ፣ የሃይማኖት ጸሎት ሲደገም "ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ..." እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም ይዘለላል ምክንያቱ ምንድን ነው?

[ ምላሽ ]
- ማማተብ !
ይህ የሚያመለክተው በጉባዔ ፣ በአደባባይ ፣ በይፋ የሚደረገውን ነው፡፡ በብዙኃን ፊት ቡራኬ መስጠት ፣ የሞተ መፍታት ፣ መስቀል ማሳለም አይፈቀድም፡፡ ይህም ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን ዓለም በማእሠረ ሰይጣን እንዳለ ፣ በግዞት በመርገም ውስጥ እንደነበረ ለማስታወስ ነው እንጂ ማዕዳችሁን አትባርኩ የሚል ሥርዓት አልተደነገገም፡፡
በግሉ አንድ ሰው ፊቱን በትእምርተ መስቀል አማትቦ መጸለይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ካላማተበ የአጋንንትን ውጊያ ድል መንሣት አይችልም፡፡ ስለዚህ በግል ጸሎት አታማትብ አይባልም፡፡ አይከለከልም፡፡
- ጸሎት !
የሃይማኖት ጸሎትም ሲደገም ፦ "ስለ እኛ ተሰቀለ ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ፣ ሞተ ፣ ተቀበረ ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ" እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም "ሐመ" ብለው ይተውታል፡፡ ይሄ ታሪኩን ለማስታወስ ነው፡፡ ጸሎቱ የሚከለከል ሆኖ አይደለም፡፡ ወቅቱን እየጠበቅን ድርጊቱን ለማስተማር ነው፡፡ ይኸውም ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ ፤ ሐሙስ መከሩ ከሐሙስ እስከ ዓርብ ሌሊት መከራውን ተቀበለ ፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይ ተሰቀለ እንላለን ፤ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ "ሞተ ተቀበረ" ይባላል፡፡ "ተነሣ" የምንለው ደግሞ ቅዳሜ በሌሊት ስድስት ሰዓት ነው፡፡ ያንን በየሰዓቱ የተደረገውን ታሪክ ለማስታወስ ፣ ለመግለጽ ፣ ለማስተማር ነው፡፡
መልክዐ መልኮች አለመደገማቸው ደግሞ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ነው፡፡ ነገረ መስቀሉ ከሁሉ በላይ ነውና፡፡ ዓለም የዳነው በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካሳነት ነው ፤ ይህንን የምናስታውስበት በስሙነ ሕማማት የእርሱን ካሳነት በፍጹም ተመስጦ እናስባለን እንጸልያለን፡፡ በዚህ ወቅት በቂ ጊዜ ስለማይኖር ወደ ቅዱሳን ገድል ትሩፋት ድጋም [ጸሎት ፣ ንባብ] አንሄድም፡፡
ነገር ግን ጊዜ ከተገኘ በሕማማት ቢሆን የቅዱሳንን ገድሎች እናነባቸዋለን፡፡ የሰዓት ቁጠባ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ግብረ ሕማማቱ እራሱ በየሰዓቱ የተዘጋጀ የራሱ ጸሎት አለው፡፡ በእረፍት ሰዓት ግን ገድሎችንም ሆነ ስንክሳርን እናነባለን፡፡ ከሰዓት አንጻር የሚታይ ነው፡፡ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ሕማሙን ሞቱን መከራውን ለእኛ ያደረገውን ካሳ በስሙነ ሕማማት በፍጹም ልቡና ለማሰብ ቅድሚያ ለእርሱ እንዲሰጥ ነው፡፡
[አንድ ጥያቄ አለኝ መለከት ቁጥር አንድ መጽሐፍ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፣ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
ይቆየን !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬