የምትፈልገኝ ሳስፈልግህ
ብቻ ከሆነ አታስፈልገኝም!
ልወድቅ ስንገዳገድ ትንሽ ድጋፍን ስሻ፣
ከጎኔ ነው ያልኩት ሰው ይነፍገኛል ትከሻ።
የሆነ ቀን ከመንገድ ላይ ወድቄ ሲመለከት፣
አዛኝ መስሎ ይቀርበኛል ተስፋ ካጣሁበት።
ለይስሙላም ያህል ሊያነሳኝ ይቃጣል፣
ግና ምን ዋጋ አለው ሰአቱ ተላልፏል።
አካሌን ደግፎ ቀና ቢያደርገኝም፣
ሰባራ ስሜቴን አይጠግንልኝም።
የዘገየ ፍቅር ይሄ ነው ችግሩ፣
ሞቼ ስቀበር ነው ሁሉም የሚንጫጫ ሲጫነኝ አፈሩ።
በህይወት ሳለሁኝ አቅም ባጣው ወራት ያልቀረቡኝ ሁሉ፣
በቀብሬ ቀን ማልደው ጉንጉን አበቦችን ይዘው ይመጣሉ።
ያኔ ነው የሚያመው ያስመሳዮች ግብር፣
ሊያክሙኝ ግዜ አጥተው ሲመጡ. . ለ ቀ ብ ር. . !
#....
ብቻ ከሆነ አታስፈልገኝም!
ልወድቅ ስንገዳገድ ትንሽ ድጋፍን ስሻ፣
ከጎኔ ነው ያልኩት ሰው ይነፍገኛል ትከሻ።
የሆነ ቀን ከመንገድ ላይ ወድቄ ሲመለከት፣
አዛኝ መስሎ ይቀርበኛል ተስፋ ካጣሁበት።
ለይስሙላም ያህል ሊያነሳኝ ይቃጣል፣
ግና ምን ዋጋ አለው ሰአቱ ተላልፏል።
አካሌን ደግፎ ቀና ቢያደርገኝም፣
ሰባራ ስሜቴን አይጠግንልኝም።
የዘገየ ፍቅር ይሄ ነው ችግሩ፣
ሞቼ ስቀበር ነው ሁሉም የሚንጫጫ ሲጫነኝ አፈሩ።
በህይወት ሳለሁኝ አቅም ባጣው ወራት ያልቀረቡኝ ሁሉ፣
በቀብሬ ቀን ማልደው ጉንጉን አበቦችን ይዘው ይመጣሉ።
ያኔ ነው የሚያመው ያስመሳዮች ግብር፣
ሊያክሙኝ ግዜ አጥተው ሲመጡ. . ለ ቀ ብ ር. . !
#....