የኔ ደብዳቤ💌


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


እማ ለውለታሽ ውለታ ምከፍለው ባይኖረኝም
ግን አንድ ቀን አኮራሻለው love u mom
contact & cross👉 @Se_c_re_t & @Mis_taa

✨ ма guy's piс

✨ воice😍

✨ videо 📹 Az
✨ amazing letter 👌🙌

✨ л💓в ече💖❣️
so join & shear this 🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ብዙ ከሚመስለኝ ግን ትንሽ ከሆነ እድሜዬ ብዙ ተምሪያለሁ ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን የህይወት ውጣ ውረዶች አይነት እና ከውጣ ውረዶቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጂ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምርያለሁ ...

To me...🎂


....እየሮጠ የመሰለኝ ጉልበቴ በድካም ዝሎ መቆሙን የዘነጋሁበት የሆነ ጊዜ ነበር...መፍጠን ከመፈለጌ የተነሳ መዘግየቴን የረሳሁበት....
#..🧚‍♀




እንደራከኝ ሳስብ ነው የምትናፍቀኝ....


የህይወት ፅንፍ ሞት
የፍቅር ደግሞ ጥላቻ ይመስለኝ ነበር....
የፍቅር ፅንፍ መተው ነው...ትውት ማድረግ....ዝም መባል...መረሳት ወድያ ወዲህ መጎተት ነፍስን ልብን ማሰቃየት ...ቀልብን ከራስ ማኳረፍ...መንፈስን ከእግዜር ማጣላት...
የፍቅር አንፃሩ ጥላቻ አይደለም መተው ነው ት ው ት ማድረግ. . . .

#... 🥀


ብቻህን መሆንን መማር አለብህ.....

...ስለዚህ የትኛውም ጓደኝነት አማራጭ እንጂ የግድ አስፈላጊ አይሆንም...


#...😇


ትዝታህ ረቂቅ ያለ ግዜው ደራሽ
እስከ መጨረሻው ሰው አስጠላኝ ጭራሽ. . .🥀


ዝም ስል የረሳውህ ይመስለኛል እንጂ ገና ነኝ አልዳንኩም .. . .


እንደጎደልክብኝ በምን እንዳነስኩብህ አላውቅም ከማናውቀው ነገ የትናንት ታሪካችን ዛሬ ከማነሴ ይገዝፋል?

#. . .🥀


ላፈቀረ... ናፍቆት ነው ወይንስ ሞት የተሻለ የሚሆነው...??
    በእርግጥ እንደኔ ሁለቱም ሞት ናቸው ልዩነቱ ናፍቆት በጊዜ የሚሽር መሆኑ ብቻ ይመስለኛል...እኔ ናፍቀኸኛል ብዬ ሳላይህ ማደር አይሆንልኝም..ሳላገኝህ ነግቶ ሲመሽ የመቻል አቅም ካለኝ የመናፈቅ ስሜት ላይ አይደለሁም ማለት ነው..
  እኔ... ስትናፍቀኝ ብዙ ወረቀቶች ያንተን ስም ከትበው በሰፈሩት ስንኞች ስግስግ ውስጥ ጠረንህ ታምቆ ብዙ ቀን ብዙ ምሽት እስክትመጣ ልቤን ላባብል ከጨረቃ መንደር ተጉዣለሁ..ካልመጣህ ካላየኸኝ ደህና የማልሆንባቸው ሺ ምክንያቶች አሉኝ..አንዳንዴ በአለሜ ላይ ፈጥሬህ እያኖርኩህ ይመስለኛል..በአለሜ ላይ መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በአንተ የሚመሰሉ ይመስሉኛል..አንተን ማፍቀር አይደክምም..ተስፋ ማድረግ አይደክምም መጠበቁም አሰልቺ አይሆንም..ለኔ ከባድ የሆነብኝ ናፍቆቱ ነው ሞትን የሚያስንቅ መናፈቅ....

      #....


''ህይወት የምታምረው ከፊት ተስፋ ከኋላም ትዝታ ሲኖራት ነው''.....
ዛሬዬ የተሰራው በሱ ትናንትናዬ ውስጥ መኖር ነው ....ታድያ ዛሬ ባይሆን እንኳ ነገዬ ላይ እንዲኖርልኝ መፈለጌ ስህተት ነው?.....

#....


ያጣናቸው ሰዎች ከላያችን ላይ ቦጭቀው የሚወስዱብን ነገር አለ።በመሄዳቸው ያጎሉብናል። እነዚህ ጉድለቶች ቀን በገፋ ቁጥር ልብ ላይ ዘልቀው የሚፈጥሩት ህመም በቀላሉ አይሽርም። ወደ ውስጥ በተመለከትን ቁጥር ጎዶሎነታችን ላይ የምንደርስበት ሰዎች አለን። በራሱ ጨለማ ተውጦ የማያውቅ ማነው?.... አመታት ቢያልፉም እንደ አዲስ የምናለቅስለት ሰው አናጣም። ይህ ስቃያችን በጎጇችን ሰላም፤ በመኝታችን ደግሞ እንቅልፍ ይከለክለናል ....

ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?


በህይወትህ ጠባቂ ስትሆን ብዙ ነገር ይገባሀል… በጣም ብዙ ነገር…ግን ከሁሉም በላይ ምን ይገባሀል መሰለህ… ጠባቂ ስትሆን አታማርም…ሁሌም ተመስገን ነው እምትለው! …ምክንያቱም ያ እምጠብቀው ቀን በማመስገን ውስጥ ነው እና እምታገኘው…


#Mis_s... 😊


. . . . ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን. . . ጨረቃንና ፀሐይን በልቅ ሰማይ ያቆመ. . .ከዋክብቶችን በጠራ ሰማይ የበተነ ሰውን ከአፈርና ከውሃ ቀይጦ የሰራ. . .ነፍስን የሰጠ . . እርሱ የሰማይ የምድር ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን!😊

#...


ያለህ አማራጭ ጠንካራ መሆን ብቻ ነው....

     #Mis_s... 😊


የምትፈልገኝ ሳስፈልግህ
ብቻ ከሆነ አታስፈልገኝም!

ልወድቅ ስንገዳገድ ትንሽ ድጋፍን ስሻ፣
ከጎኔ ነው ያልኩት ሰው ይነፍገኛል ትከሻ።
የሆነ ቀን ከመንገድ ላይ ወድቄ ሲመለከት፣
አዛኝ መስሎ ይቀርበኛል ተስፋ ካጣሁበት።
ለይስሙላም ያህል ሊያነሳኝ ይቃጣል፣
ግና ምን ዋጋ አለው ሰአቱ ተላልፏል።
አካሌን ደግፎ ቀና ቢያደርገኝም፣
ሰባራ ስሜቴን አይጠግንልኝም።
የዘገየ ፍቅር ይሄ ነው ችግሩ፣
ሞቼ ስቀበር ነው ሁሉም የሚንጫጫ ሲጫነኝ አፈሩ።
በህይወት ሳለሁኝ አቅም ባጣው ወራት ያልቀረቡኝ ሁሉ፣
በቀብሬ ቀን ማልደው ጉንጉን አበቦችን ይዘው ይመጣሉ።
ያኔ ነው የሚያመው ያስመሳዮች ግብር፣
ሊያክሙኝ ግዜ አጥተው ሲመጡ. . ለ ቀ ብ ር. . !

#....


...
ብቻ አንዳንዴም ከአለም ተነጥሎ..... ከሁሉ ጨዋታ ውጭ ሆኖ.. የሆነኛውን ጥግ ይዞ ሁሉን መታዘብና ለልብ የአዘቦት ቀንን መስጠት የሆነ ያህል እረፍት አለው. . .🥀
#Mis_s... 🥀


በኖርኩባቸው ጥቂት አመታት ውስጥ በርካታ ነገሮች አይቻለው.... በቸርነትህ እና በምህረትህ ጠብቀህ ለዚች ቀን ላበቃኸኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረስህ ....ባለፈው ዘመኔ የሆነው ሁሉ እንኳን ሆነ ያልሆነው ሁሉ እንኳን ቀረ ስለተጨመረልኝ እድሜ እግዚአብሔር ይመስገን🙏.. ለምትወዱኝ እንኳን ተወለድኩላቹ መልካም ልደት ለኔ🥰....

#Mis_s... 🧚‍♀


እኔ አላለቀስኩም. . .አለቀሳችሁ እንዴ?....

#.... 🥀


ስነካህ እወድሃለሁ ማለቴ ነው. . .

Показано 20 последних публикаций.