ላፈቀረ... ናፍቆት ነው ወይንስ ሞት የተሻለ የሚሆነው...??
በእርግጥ እንደኔ ሁለቱም ሞት ናቸው ልዩነቱ ናፍቆት በጊዜ የሚሽር መሆኑ ብቻ ይመስለኛል...እኔ ናፍቀኸኛል ብዬ ሳላይህ ማደር አይሆንልኝም..ሳላገኝህ ነግቶ ሲመሽ የመቻል አቅም ካለኝ የመናፈቅ ስሜት ላይ አይደለሁም ማለት ነው..
እኔ... ስትናፍቀኝ ብዙ ወረቀቶች ያንተን ስም ከትበው በሰፈሩት ስንኞች ስግስግ ውስጥ ጠረንህ ታምቆ ብዙ ቀን ብዙ ምሽት እስክትመጣ ልቤን ላባብል ከጨረቃ መንደር ተጉዣለሁ..ካልመጣህ ካላየኸኝ ደህና የማልሆንባቸው ሺ ምክንያቶች አሉኝ..አንዳንዴ በአለሜ ላይ ፈጥሬህ እያኖርኩህ ይመስለኛል..በአለሜ ላይ መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በአንተ የሚመሰሉ ይመስሉኛል..አንተን ማፍቀር አይደክምም..ተስፋ ማድረግ አይደክምም መጠበቁም አሰልቺ አይሆንም..ለኔ ከባድ የሆነብኝ ናፍቆቱ ነው ሞትን የሚያስንቅ መናፈቅ....
#....