ለውጪ ሃገር ሥራ ሥምሪት ማሰልጠን ለምትፈልጉ አካላት በሙሉ!
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በሰለጠነና በከፊል በሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ ተለያዩ ሃገራት ዜጎች በቂ ስልጠናና ክህሎት አግኝተው እንዲሰማሩ በማድረግ ደህንነታቸው፣ መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በመሆኑም መንግስት ለዜግችን ለማሰልጠን ዝግጁ አድርጎ ዜጎችን በማሰልጠን ላይ ከሚገኙ ከ100 በላይ ፓሊ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በተጨማሪ የግል ተቋማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ስታንዳርድ በማዘጋጀት በዚህ ስታንዳርድ መሠረት ማሰልጠን እችላለሁ የሚል ማንኛውም አካል ተገቢውን ሰነድ በሟሟላት ማሰልጠን የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን። ለዚህም የሚያስፈልገው ስታንዳርድ ለሁሉም ክልልና ከተማ መስተዳድር የተሰጠ በመሆኑ ስታንዳርዱን ከክልልና ከተማ መስተዳድር በመውሰድ የቴክኖሎጂ አክሰስ ደግሞ ከሥራና ክህሎት ሚኒስትር በመውሰድ ዜጎችን ማሰልጠን የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
በዚህ ውጤታማ የውጪ ሃገር ሥራ ሥምሪት ዜጎቻችን ለሥራ ሲሰማሩ በዘላቂነት ህይወታቸው እንዲቀየር፣ የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈፀመባቸው ሃገራት መካከል ለሚኖረው ጠንካራ ግንኙነት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች መሆን እንዲችሉ ማስቻል፣ ዜጎች ከስደት ወይም ከእለት ጉርስ ባለፈ ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል የሁላችንም ሃገራዊ ሃላፊነት ነው!