ቅንጅት ለላቀ የሥራ ስኬት!
ለሃገር አቀፍ የግብርና ናሙና ቆጠራ በቴክኖሎጂ ታግዞ የተደረገው የሰው ሃይል ምልመላን በተመለከተ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መስሪያቤታችን ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር በከር ሻሌ (ዶ/ር) ጋር እንዲሁም ከሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የምልመላ ሂደቱን በተመለከተ ግምገማ አድርገናል።
በሚኒስትር መስሪያቤታችን ስር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS ሲስተም በኩል 43,500 ሰራተኞችን ለመመልመል በታቀደው መሰረት በአምስት የሥራ ቀናት ብቻ ከ200 ሺህ በላይ አመልካች የተመዘገበ ሲሆን በቴክኖሎጂው ትሩፋት ከአድሎአዊ አሰራር የፀዳ፣ ቀልጣፋና ግዜን እንዲሁም ጉልበትን ቆጣቢ የሆነ የምልመላ ሂደስ መታየቱ በቀጣይ በቅንጅት ለምንሰራቸው ሥራዎች የላቀ የራስ መተማመንን አጎናፅፎናል።
ምልመላውን ልዩ የሚያደርገው በኢትዮጵያ ወይም በአዲስ አበባ ተብሎ የሚጠቀስ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች ላይ እያንዳንዱን ቀበሌ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተከናወነ መሆኑ ምልመላውን ከባድ ያደርገዋል። በዚህም መሠረት የሥራ መሥፈርቱን ያሟሉ 73,000 እጩ አመልካቾች ወደ ቀጣዩ ፈተና ተዘዋውረዋል። በቀጣይም በስልካቸው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በሚደርሳቸው የፅሁፍ ፈተና ለሥራው ብቁ የሆኑትን የምንለይ ይሆናል።
ይህን የቅጥር ሂደት በአነስተኛ ወጪ፣ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ብቁ ሠራተኛ በዚህ ከፍተኛ የሰው ሃይል ቁጥር ልክ ማቅረብ መቻሉ በተጨማሪም ቀጣሪም ሆነ አመልካች ሳይጉላላ ጥራት ያለው አገልግሎት መሥጠት መቻሉ ትልቅ ስኬትና የሥራችን ውጤት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
ነሐሴ 9/2016 ግ.ም