💙 የጥያቄዎች መልስ ክፍል 77 💙
▶️፩. "መንፈስም መጣ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እኔ አታልለዋለሁ አለ። እግዚአብሔርም በምን ታታልለዋለህ አለው። እርሱም ወጥቼ በነቢያት ሁሉ አፍ የሐሰትን መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም ታታልለዋለህ ይቀናሃል ውጣ እንዲህም አድርግ አለው ሲል መንፈስ በእግዚአብሔር ፊት በምን መልኩ ነው የሚቆመው? እግዚአብሔር ሰዎችን እንዲያታልል ሥልጣን ይሰጣል ወይ?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ አለ ይኖራል። መንፈስ የተባለ ከዚህ ሰይጣን ነው። ሰይጣን ግን ውሱን ስለሆነ በሁሉ ቦታ አይገኝም። ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ቆመ መባሉ ሐሳቡ በእግዚአብሔር መታወቁን መግለጽ ነው። እግዚአብሔር ሰይጣንን ይቀናሃል ውጣ ማለቱ አምላኬ ከሕዝቡ ረድኤቱን መንሣቱን መግለጽ ነው እንጂ ክፋትን ፈቃጅ ሆኖ አይደለም። እግዚአብሔር ከሕዝቡ ረድኤቱን ከነሣ ሰይጣን እንደሚያታልላቸው ለማሳወቅ የተነገረ ቃል ነው።
▶️፪. 2ኛ ዜና መዋ.16፥12 ላይ አሳ ባለመድኃኒቶችን መፈለጉ ጥፋት ከሆነ እኛም ፈውስ ሽተን ሐኪም እንልጋለን። ይህስ ጥፋት ይሆን? አሳስ ባለመድኃኒት መፈለጉ ስለምን ጥፋት ሆነበት?
✔️መልስ፦ ከዚህ አሳ የተወቀሰው በእግዚአብሔር መታመኑን ትቶ በሰዎች በመታመኑ ነው። እንጂ እግዚአብሔርን አምነውና በእግዚአብሔር ታምነው በዶክተሮች መታከም ችግር የለውም። ለእነርሱም ጥበብን የገለጠ እግዚአብሔር ነውና።
▶️፫. በእግዚአብሔር መታመን እና በምድራዊ ነገር መታመን ልዩነቱ? ጥፋት የሚሆንበት እና የማይሆንበትስ መንገድ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ በእግዚአብሔር መታመን የሚያኖረን እግዚአብሔር እንደሆነ በሙሉ ልብ ተቀብሎ መኖር ነው። በምድራዊ ነገር መታመን ማለት ደግሞ ሰው እግዚአብሔርን ትቶ በፍጡራን ሲታመንና ፍጡራንን ሲፈራ ነው።
▶️፬. 2ኛ ዜና መዋ.17፥16 ማስያስ ማለት መሢህ ማለት ነው አይደል? እንዴት በብሉይ ኪዳን ተገኘ?
✔️መልስ፦ በስም መመሳሰል ነው እንጂ መሢሁ በዚያ ጊዜ ስለተወለደ አይደለም። በብሉይ ኢያሱ ማለት መድኃኒት ነው። ክርስቶስን ኢየሱስ ስንለውም መድኃኒት ማለታችን ነው። ነገር ግን ኢያሱን መድኃኒት ስንለው የጸጋ ሲሆን ክርስቶስን መድኃኒት ስንለው ግን የባሕርይ ነው። በዚህ መሠረት በብሉይ ማአስያስ ሲባል የጸጋ መሆኑን መገንዘብ አለብን። ክርስቶስን መሢሕ ስንለው ግን የባሕርይ ንጉሥ መሆኑን ለመግለጽ ነው።
▶️፭. 2ኛ ዜና መዋ.18፥26 የመከራ እንጀራ እና የመከራ ውኃ ሲል ምን ማለቱ ነው?
✔️መልስ፦ በጭንቅ ጊዜ የሚመገቡትን እንጀራ የመከራ እንጀራ ሲለው የሚጠጡትን ውሃውን ደግሞ የመከራ ውኃ ብሎታል።
▶️፮. 2ኛ ዜና መዋ.20፥5 ላይ ኢዮሣፍጥ የጸለየው ጸሎት አለ። የጦርነቱም ውጤት ከታች ተዘርዝሯል። ስለዚህ በጸሎቱ ነው የሆነለት ማለት እንችላለን? እኛስ በነገሮች ሁሉ በጸሎቴ ነው ይሄ የሆነልኝ፣ ካልጸለይኩ አይሆንልኝም እያልን የምንጠቀመው አገላለጽ ትክክል ነውን?
✔️መልስ፦ በጸሎቱም በእግዚአብሔር ረድኤትም ነው። ሰው ያለ እግዚአብሔር ረድኤት በጸሎቱ ብቻ ምንም ማድረግ አይችልም። ረድኤተ እግዚአብሔርም በጸሎት ይሰጣል እንጂ እጅን አጣጥፎ ቁጭ ብሎ ይረዳኛል ማለት አምላክን መፈታተን ነው። ስለዚህ መጸለይም ይገባል፣ ረድኤተ እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግም ይገባል።
▶️፯. የይሁዳና የእስራኤል ንጉሥ እያለ እየለያየ የሚናገረው ለምንድን ነው? ይሁዳ እስራኤል ውስጥ ሳለች ለምን ነገሥታቱስ ተለያዩ?
✔️መልስ፦ እስራኤላውያን ለሁለት ተከፍለው ሁለት ሀገር ሆነው ነበረ። አንዲቱ ሀገር ስሟን በቀድሞው ሰይማ እስራኤል ተባለች። አንዷ ደግሞ ይሁዳ ተባለች። ስለዚህ የተለያዩ ሀገሮች ስለሆኑ እየለያየ ተናግሯል።
▶️፰. "ኢዮሳፍጥ ግን እንጠይቀው ዘንድ የእግዚአብሔር ነቢይ የኾነ ሌላ ሰው በዚህ አይገኝምን አለ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.18፥6)። ኢዮሳፍጥ እንዲህ ያለው ሐሰተኛ ነቢያት እንደሆኑ አውቆ ነው?
✔️መልስ፦ ነገሥታት ከእግዚአብሔር ረድኤትን ለማግኘት ነቢያትን ያማክሩ ነበረ። ስለዚህ እውነተኛ ነቢይ ፈልጎ አለ ወይ ብሏል። ሌሎቹ ሐሰተኛ ነቢያት እንደሆኑ እንዳወቀ ከዚሁ ጥቅስ ቀደም ብሎ ተገልጿል።
▶️፱. "እግዚአብሔርም ወጥቶ በሬማት ዘገለአድ ይወድቅ ዘንድ የእስራኤልን ንጉሥ አክአብን የሚያታልል ማን ነው? አለ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.18፥19)። ይህን ያለው ለማን ነው?
✔️መልስ፦ ለሰይጣን እንደሆነ ዝቅ ብሎ ተገልጿል። እግዚአብሔር የሰይጣንን ሐሳብ ቀድሞ ስላወቀው የሰይጣንን ክፉ ሐሳብ ቀጣዩ ትውልድ ያውቅ ዘንድ ምን እንደሚለው እያወቀ ጠይቆታል።
▶️፲. "የእስራኤል ንጉሥ ከነቢያት አራት መቶ ሰዎች ሰብስቦ" ይላል (2ኛ ዜና መዋ.18፥4)። በወቅቱ ይሄን ያህል የሐሰተኛ ነቢያት መነሣት ምክንያቱ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ሐሰተኛ ነቢያት በየዘመናቱ ይነሣሉ። ይህ ሁሉ ለመነሣቱ ምክንያቱ ራሳቸው ሐሰተኞች ነቢያት ናቸው። ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ራሳቸውን የእውነት ሳይሆን የሐሰት አገልጋይ ስላደረጉ ነው ምክንያቱ።
▶️፲፩. "ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ ሚክያስ ሆይ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንኺድን ወይስ እንቅር አለው። እርሱም ውጣ ተከናወን በእጅኽም ዐልፈው ይሰጣሉ አለ። ነገር ግን ወደ ሰልፍ ከወጡ እንደሚሸነፉ አልነበረም? ለምንድን ነው በእጅኽም ዐልፈው ይሰጣሉ ያለው?
✔️መልስ፦ ነቢዩ ሚክያስ መጀመሪያ የተናገረው በምጸት ዘይቤ ነው። ምጸት ዘይቤ ደግሞ በተቃራኒው ይተረጎማል። ሁለተኛ ግን በትሕትና ሆነው ቢለምኑት እንደሚሸነፉ ገለጾላቸዋል።
▶️፲፪. “አሁንም ልከህ እስራኤልን ሁሉ፥ በኤልዛቤልም ማዕድ የሚበሉትን አራት መቶ አምሳ የበኣልን ነቢያት፥ አራት መቶም የማምለኪያ አፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ አለ” ይላል (1ኛ ነገ.18፥19)። እንዲሁ “የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ ሰዎች ሰብስቦ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር? አላቸው። እርሱም እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ አሉት” ይላል (2ኛ ዜና መዋ.18፥5)። ዜና መዋዕል ላይ የተጠቀሰው የሐሰት ነቢያት ቁጥር 400 ሲሆን ነገሥት ላይ የተጠቀሰው ግን 450 ነው። ወይስ ነገሥት ላይ ያለውን የማምለኪያ አፀድ ነቢያትን ለማለት ተፈልጎ ነው? በበኣል ነቢያት እና በማምለኪያ አፀድ ነቢያት መካከልስ ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ዜና መዋዕል የማምለኪያ አፀድ ነቢያትን ቆጥሮ 400 አለ። ነገሥት የበአል ነቢያትን ቆጥሮ 450 አለ። በበኣል ነቢያትና በማምለኪያ አፀድ ነቢያት መካከል ያለው ልዩነት የቦታ ነው እንጂ ሁለቱም ጣዖትን በማምለክ አንድ ናቸው።
▶️፲፫. 2ኛ ዜና መዋ.18፥30 ላይ የሶርያ ንጉሥ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን እንጂ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሳፍጥን አትግጠሙ (አትዋጉ) ሲል 2ኛ ዜና መዋ.20፥2 ላይ ደግሞ ከሶርያ ታላቅ ሠራዊት ኢዮሳፍጥን ሊዋጋ እንደመጣ ተገልጿል። ሀሳቡ እንዴት ይታረቃል?
✔️መልስ፦ 2ኛ ዜና መዋ.18፥30 ላይ የተደረገው ጦርነትና 2ኛ ዜና መዋ.20፥2 ላይ የተደረገው ጦርነት የተለያየ ነው። በመጀመሪያው የሶርያ ጦር እስራኤልን ብቻ ወግቶ የእስራኤልን ንጉሥ ገድሎ አልፏል። በሁለተኛው ደግሞ ይሁዳን ሊገጥም መጥቷል።