▶️፲፯. "የወርቅ ቀለበት በዕሪያ አፍንጫ እንደ ሆነ ከጥበብ የተለየች ቈንዦ ሴትም እንዲሁ ናት" ይላል (ምሳ.11፥22)። ምሥጢሩ ምንድን ነው? በዕሪያ አፍንጫ የወርቅ ቀለበት እንዴት ሊገኝ ይችላል?
✔️መልስ፦ ምሥጢሩ ከጥበብ የተለየች፣ ጥበብ የሌላት ሴት አትጠቅምም አንድም አትጠቀምም ማለት ነው። ሴት ከቁንጅናዋ በተጨማሪ ጥበብ ሊኖራት ይገባል ማለት ነው። ዓረፍተ ነገሩ በዕሪያ አፍንጫ ወርቅ ይገኛል አይልም። ቢሆን ተብሎ የተገለጸ ነው። ይህም ማለት የወርቅ ቀለበት በዕሪያ አፍንጫ እንደሆነ ማለት ወርቅ በዕሪያ አጠገብ ብናስቀምጥ የወርቁ ጥራት የዕሪያውን መልክ ያሳየዋል። በዚህ ጊዜ ዕሪያው ደንግጦ ወርቁን ይረግጠዋል። በአጭሩ ፍሬ ነገሩ ለዕሪያ ወርቅ እንደማይጠቅመው ሁሉ ለቆንጆ ሴትም ጥበብ ከሌላት ቁንጅናዋ አይጠቅማትም ማለት ነው።
▶️፲፰. "ያለውን የሚበትን ሰው አለ ይጨመርለታልም። ያለቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ ይደኸያልም" ይላል (ምሳ.11፥24)። ያለውን የሚበትን ሰው እንዴት ሊጨመርለት ይችላል? ቆጥቦ መጠቀም፣ ራስን ማስተዳደር ያስኮንናል እንዴት?
✔️መልስ፦ ያለውን የሚበትን ሰው የተባለ ካለው በተቻለው መጠን የሚመጸውት ሰው ለማለት ነው። ንፉግ ሰው ግን መመጽውት ሲገባው ባለመመጽወቱ ይደኸያል ማለት ነው። ራስን ማስተዳደር፣ የዓመት ልብስን የዕለት ጉርስን ቆጥቦ መጠቀምም አያስኮንንም። ከላይ የተነገረው እየተቻለው መመጽወት የማይችል ሰው በእግዚአብሔር እንደሚቀጣ ለማመልከት ነው።
▶️፲፱. "ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጎድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል" ይላል (ምሳ.12፥9)። ለራሱ ባሪያ ሆኖ ሲልና እንጀራ ጎድሎት ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው ማለት ምንም ስለሌለው ለሌሎች ባሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሰው የአገልግሎቱን ዋጋ ስለሚያገኝ አይቸገርም ማለት ነው። እንጀራ ጎድሎት ራሱን ካከበረው የተባለው ደግሞ እኔ የመኳንንቱ፣ የነገሥታቱ፣ የታላላቆች ሰዎች ዘር ነኝ እያለ ኮርቶ የሚበላው እስከሚያጣ የሚደርስ ሰው ነው።
▶️፳. "ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል የኃጥኣን ሆድ ግን ይራባል" ይላል (ምሳ.13፥25)። የጻድቅ ሰውነት እስክትጠግብ የሚበላው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ከዚህ ጻድቅ የተባለ እያረሰ፣ እየቆፈረ፣ እየሠራ የሚኖር ሰው ነው። በደንብ የሠራ ሰው ምግቡን በደንብ ስለሚያገኝ እስኪጠግብ ይበላል ማለት ነው። በሌላ መልኩ ጻድቅ በእግዚአብሔር ጸጋ ደስ ብሎት ይኖራል ማለት ነው። የኃጥኣን ሆድ ግን ይራባል ያለው ኃጥኣን ያላቸው ከዚህ ሰነፎችን ነው። ሰነፎች ስለማይሠሩ ብዙ ንብረትና እህል አያገኙም በዚህ ምክንያት እስኪጠግቡ አይበሉም ማለት ነው። በሌላ መልኩ ኃጥኣን ሕገ እግዚአብሔርን ስለማይጠብቁ ከጸጋ እግዚአብሔር ተራቁተው ይኖራሉ ማለት ነው።
▶️፳፩. "ሁለት ምሥጢር ያለው የጉባኤ ምሥጢር ይገልጣል" ማለት ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ሁለት ምሥጢር ያለው ማለት ለአንዱ ሌላ፣ ለሌላው ሌላ የሚናገር ሰው የጉባኤውን ምሥጢር አሳልፎ ለሌሎች ያወጣል ማለት ነው። አለመታመኑን ለመግለጽ ነው። ታማኝ ሰው ለማኅበሩ ምሥጢር ብቻ ይገዛል እንጂ ለሌላው ስለማይገዛ ሁለት ምሥጢር አይኖረውም። ከሓዲ ሰው ግን ታማኝነት ስለሌለው የሌላውን ምሥጢር ለሌላው በመናገሩ ከዚህ ሁለት ምሥጢር ያለው ተብሏል።
▶️፳፪. "ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል" ማለት ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ስንዴውን የሚያደልብ ማለት መመጽወት ሲገባው ምጽዋቱን ትቶ የሚያከማች ሰው ለአሕዛብ ይተወዋል ማለት እርሱ ሞቶ ሌሎች ይወርሱታል ማለት ነው። እንዲሁም የማይመጸውትን ሰው አጋንንት ይወርሱታል ማለት ነው።
▶️፳፫. "ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰናከላሉ። ኃጥኣን በጻድቃን በር ያገለግላሉ" ሲል ምን ለማለት ነው? (ምሳ.14፥19)።
✔️መልስ፦ ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰናከላሉ ማለት በደጋጎች ሰዎች ፊት ኃጢአትን በደልን ይሠራሉ ማለት ነው። ሰብአ ትካት በኖኅ ፊት ኃጢአት እንደሠሩና በኋላ ግን በማየ አይኅ እንደጠፉ ማለት ነው። ኃጥኣን በጻድቃን በር ያገለግላሉ ማለት በጻድቃን ሰዎች ይገዛሉ ማለት ነው።
▶️፳፬. ምሳ.፲፬፥፲፫ ላይ "ከደስታ ጋር ኀዘን አይቀላቀልም። የደስታ ፍጻሜ ግን ወደ ኀዘን ይመለሳል" ሲል ምሥጢሩ ቢብራራ።
✔️መልስ፦ ደስታና ኀዘን ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ስለሆኑ አይቀላቀሉም ማለት ነው። የደስታ ፍጻሜ ወደ ኀዘን ይመለሳል የሚለው የዚህችን ዓለም ደስታ ነው። የሥጋዊ ተድላ ደስታ ፍጻሜው ኀዘን ነው ማለት ሑሩ እምኔየ (ከእኔ ሂዱ) ተብሎ ዘለዓለማዊ ኀዘን ወዳለበት ወደ ገሀነም መግባት ነው ማለት ነው።
▶️፳፭. "ልበ ጠማማዎች በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው። በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው" ይላል (ምሳ.11፥20)። እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ለምን ይጠላል? ሰውስ ፍጹም መሆን ይቻለዋልን?
✔️መልስ፦ እግዚአብሔር በባሕርይው ፍቅር ነው። ስለዚህ እርሱ ፍጥረታትን ምንም ቢያደርጉ አይጠላቸውም። ነገር ግን ሰዎች ቢበድሉ በበደላቸው ምክንያት ፈርዶ ወደ ሲዖል ወደ ገሀነም የሚያስገባቸው በመሆኑ ፍርዱን በሰውኛ ከመጥላት ቆጥሮት ነው። ሰውን ፍጹም ባለመሆኑ እግዚአብሔር አይጠላውም። ሰው ወደ ፍጹምነት ለማደግ መልካም ሥራን አብዝቶ መሥራት ግን ይገባዋል።
▶️፳፮. ምሳ.12፥13 ላይ "ድንገት በበር የሚገናኝ" ሲል ምን ለማለት ነው?
✔️መልስ፦ ድንገት በበር የሚገናኝ ያለው በጠብ ወይም በጥል የሚገናኝ ለማለት ነው። በር መተላለፊያ ነው። ጠላት በመተላለፊያ ሲገናኝ ያስደነግጣልና ነው። ግእዙ የተሻለ ገልጾታል። "ወዘሰ ይዳደቅ በአናቅጽ ያመነድብ ነፍሳተ" ይላል። ግንኙነቱ በጥል (በድድቅ) ነው።
▶️፳፯. ምሳ.12፥25 ጻድቅ ሰው በሰማው ክፋት እንዴት ይደነግጣል? በእግዚአብሔር አይተማመንምን?
✔️መልስ፦ ሰው ምንም ያህል ጻድቅ ቢሆን ድንጋጤ ይስማማዋል። ከፍጥረታት ሁሉ በላይ የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንኳ ሄሮድስ ሲያሳድዳትና ወታደሮች በመንገድ ሲያገኟት ትደነግጥ ነበርና። ይህ በእግዚአብሔር ከመተማመን ጋር አይገናኝም። አዳም ከወደቀ በኋላ የሰው ልጅ ድንጉጥ ሆኗልና።
▶️፳፰. ምሳ.14፥10 የአዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ደስታ እንጅ ኀዘን ነውን?
✔️መልስ፦ አዋቂ ሰው በዚህ ምድር ሳለ በአላዋቂዎች ንግግርና ድርጊት ማዘኑ አይቀርም። ይህን ለመግለጽ ነው። ሰው እያወቀ ሲመጣ በዚህች ምድር በሥጋው ኀዘንተኛ ነው የሚሆነው።
▶️፳፱. ምሳ.፲፩፥፲፰ ላይ "የኀጥእ ሰው ሙያ ሐሰተኛ ነው" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ኃጢአተኛ ሰው የሚሠራው ሥራ (ሙያ) ሐሰተኛ ነው ማለት ክፉ ሥራን ይሠራል ማለት ነው። በክርስትና አንድ ነገር ሐሰት ነው የሚባለው ከእግዚአብሔር ሕግ በተቃራኒ ከተተገበረ ነውና።
▶️፴. ምሳ.፲፩፥፴፩ ላይ "እነሆ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ" የሚለው ላይ ምን ማለት እንደፈለገ ቢያብራሩልን? ጻድቅ እንዴት ፍዳ ይቀበላል? ምሳ.፲፪፥፳፩ ደግሞ "ጻድቅን መከራ አያገኘውም" ይላል። ሁለቱ ጥቅሶች እንዴት ይታረቃሉ?