ኳኳኳ ኳኳኳ...
ከሌሊት እንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ደርሶ
ፈንደቅደቅ አረገኝ መልሶ መላልሶ
ምንድን ነው በሞቴ?
ምነው ቶሎ ነጋ ዛሬስ ያለአመሉ
ይሄን መሳይ ዜማ
ከወዴት ቀድተውት ወፎች ሲሉት ዋሉ🤔
ምን እንዲህ አስዋባት
ምንስ አጣደፋት ፀሀዩኣ ልትወጣ
የምር ተሰምቶኛል?
ወይስ ጆሮየ ነው ንፋስ ሳቅ አወጣ?
ቤቴ ብርሀን ሞላ ውብ በአካል ተገኘ
የደጃፌ አበቦች መአዛቸው ናኘ
ደማምቋል ሰፈሩ
ድግስ እንዳለባት ደርባባ ወይዘሮ
ሁሉ አምሮባቸዋል
እኔስ አልገባኝም ምን አለ ዘንድሮ?
የእነሱ ሲገርመኝ
አይኔ ሌሊት ነቅቶ ንጋቱን ያስሳል
ጆሮዬ በሌሊት ምስራች ሊሰማ ለሩቅ ይቀስራል
እጅና እግሮቼ ይቁነጠነጣሉ
መምጫቸውን እንጃ ካልሄድን ይላሉ
ልቤ ጉጉት ወርሶት ምቱ ይፋጠናል
ሀሳቤ ለውበት መልክሽን ያጠናል
ጥርሴ በጠዋቱ ይስላል ፈገግታ
ቀልቤ ገና በሌት ይገባል እስክስታ
ወዳንቺ አጣደፈኝ
ዙሪያየ በሙሉ በመልክሽ ተሞላ
ምንም ሳያቅማማ
ለእኔ ሳያዝንልኝ ሁሉ ላንቺ አደላ
አበባው ወፎቹ መንደሩም ወዳጅሽ
አንቺን አንቺን አሉኝ ሸኙኝ እስከደጅሽ
ምን ሆነዋልሳ
ፀሀይም ጨረቃም እስክደርስ ያጀቡኝ
ጉበት ሀሞት ጣፊያ ቅብጥርሴ ሁሉ
ላይሽ ያዋከቡኝ
ምን ነካቸው ዛሬ? አዲስ ጉድ አለ እንዴ?🤔
አሁን ምን ይሉታል
ይሄን ሀሳብ መያዝ ይሄን ማሰላሰል
እንዲህ ውብ ከሆነ
እንደው ጠረጠርኩት ልደትሽ ነው መሰል😳
ልክ ነኝ አይደል?😁
መልካም ልደት❤️🥳
26 - 05 - 2017 ዓ.ም
በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
ከሌሊት እንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ደርሶ
ፈንደቅደቅ አረገኝ መልሶ መላልሶ
ምንድን ነው በሞቴ?
ምነው ቶሎ ነጋ ዛሬስ ያለአመሉ
ይሄን መሳይ ዜማ
ከወዴት ቀድተውት ወፎች ሲሉት ዋሉ🤔
ምን እንዲህ አስዋባት
ምንስ አጣደፋት ፀሀዩኣ ልትወጣ
የምር ተሰምቶኛል?
ወይስ ጆሮየ ነው ንፋስ ሳቅ አወጣ?
ቤቴ ብርሀን ሞላ ውብ በአካል ተገኘ
የደጃፌ አበቦች መአዛቸው ናኘ
ደማምቋል ሰፈሩ
ድግስ እንዳለባት ደርባባ ወይዘሮ
ሁሉ አምሮባቸዋል
እኔስ አልገባኝም ምን አለ ዘንድሮ?
የእነሱ ሲገርመኝ
አይኔ ሌሊት ነቅቶ ንጋቱን ያስሳል
ጆሮዬ በሌሊት ምስራች ሊሰማ ለሩቅ ይቀስራል
እጅና እግሮቼ ይቁነጠነጣሉ
መምጫቸውን እንጃ ካልሄድን ይላሉ
ልቤ ጉጉት ወርሶት ምቱ ይፋጠናል
ሀሳቤ ለውበት መልክሽን ያጠናል
ጥርሴ በጠዋቱ ይስላል ፈገግታ
ቀልቤ ገና በሌት ይገባል እስክስታ
ወዳንቺ አጣደፈኝ
ዙሪያየ በሙሉ በመልክሽ ተሞላ
ምንም ሳያቅማማ
ለእኔ ሳያዝንልኝ ሁሉ ላንቺ አደላ
አበባው ወፎቹ መንደሩም ወዳጅሽ
አንቺን አንቺን አሉኝ ሸኙኝ እስከደጅሽ
ምን ሆነዋልሳ
ፀሀይም ጨረቃም እስክደርስ ያጀቡኝ
ጉበት ሀሞት ጣፊያ ቅብጥርሴ ሁሉ
ላይሽ ያዋከቡኝ
ምን ነካቸው ዛሬ? አዲስ ጉድ አለ እንዴ?🤔
አሁን ምን ይሉታል
ይሄን ሀሳብ መያዝ ይሄን ማሰላሰል
እንዲህ ውብ ከሆነ
እንደው ጠረጠርኩት ልደትሽ ነው መሰል😳
ልክ ነኝ አይደል?😁
መልካም ልደት❤️🥳
26 - 05 - 2017 ዓ.ም
በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19