በያ ልበልሻ
(እጅግ የሚያስተክዝ ታሪክ)
(በእውቀቱ ስዩም)
የሆነ ጊዜ ላይ ብቸኝነት በጣም ተሰማኝ፤ አንድ የስነልቦና ሊቅ ብቸኝነት በጽኑ ከተሰማህ ዛፍም ቢሆን እቀፍ የሚል ምክር ይለግሳል፤ ማቀፍ መድሀኒት ነው! እኛ ሰፈር የነበረው ትልቅ የግራር ዛፍ ኮሪደሩ ሲለማ መገርሰሱን ደረስኩበት፤ እንግዲህ ማንን ልቀፍ? ዛፉን የገረሰሰውን ዶዘር ማቀፍ አማረኝ::
በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ አንድ ቀን ማታ ላይ መነን ደወለችልኝ፤
“እንዴት ነህ?”
ያለሁበትን ሁኔታ አስረዳሁዋት፤
“ አጠገብህ ሆኘ ባቅፍህ ደስ ይለኝ ነበር ! ግን አልቻልኩም”
“ እድሌ ነው”
“ አሁን የት ነው ያለኸው?”
“ ሳሎን “
“ምኝታ ቤት ግባ”
ገባሁ፤
“ የምትወደውን ለስለስ ያለ ሙዚቃ ክፈት “
በላፕቶፔ The last of the mochians ሳውንድ ትራክ ከፈትኩ፤
“ምን ለብሰሀል?”
“ ቱታ”
“ እኔ እንደማወልቅልህ እያብክ ቀስ አድርገህ አውልቀው”
በጣም ስሜታዊ ስለሆንኩ ቱታውን ማውለቅ ጊዜ ወሰደብኝ፤
“አወለቅህ?”
“እየታገልኩ ነው”
“ የጋራዥ ቱታ ነው እንዴ የለበስከው?”
“ አሁን አወለቅሁ
”
“ምን ቀረ?
“ ቲሸርት እና እና ሙታንታ “
“ አውልቅ”
“ አወለቅሁ”
“ ጥሩ ! “ አለች መነን “ አሁን ያወለቅኸውን ሰብሰበህ፤ ሳፋና ኦሞ ፈልገህ ሙልጭ አድርገህ እጠበው! ድብርቱ ይለቅሀል!"
2
ጥቂት ወራት ዞር ዞር ብየ ወደ ሸገር ተመለስኩ፤
ደወለችና የባጥ የኮርኔሱን አውርተን
“ምን አመጣህልኝ? “አለችኝ ፤
“ አምሳ ማስቲካ ፤ አራት ሽቶ፤ ስድስት ቅባት፤ አስራሁለት ቪታሚን እና ቸኮሌት ገዝቼልሽ ነበር፤ “
“ነበር?”
“ ሻንጣየን ያደራጁልኝ ዘመዶቼ ያንቺን እቃ ረስተው ሳይጭኑልኝ ቀሩ “
“በጣም ነው የምታናድደው “ ጮኸችብኝ ፤
“ አትቆጪ! ጉዋደኛየ በቅርቡ ስለሚመጣ ይዞልኝ እንዲመጣ ቃል ገብቶልኛል !”
”መች ነው እሚመጣው?”
“ከተሳካለት በቅርብ ይገባል “
“ ማን ነው እሱ?”
“ልደቱ አያሌው ይባላል”
ስልኩን ከመዝጋት ውጭ አማራጭ አልነበራትም፤ አጠገቤ ብትሆን ኖሮ የሽንት እና የእስትንፋስ ቧንቧየን ነበር አስተባብራ የምትዘጋው!
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19