✨✨✨በ'ነሱ ቤት✨✨✨
✨✨✨ክፍል አንድ✨✨✨
አንዲት አነስተኛ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ ሦስት አብሮ አደግ ጓደኛሞች የጦፈ ወሬ ይዘዋል ። ሦስቱም በአካባቢው ላይ አላቸው ከተባሉ አብታም ቤተሰቦች ነው የተገኙት ። ከችግር ከአሳብ ከጭንቀት ነፃ ሆነው ነው ያደጉት ። በእነሱ ቤት አሳቢው ነገሮችን ማስተካከል ያለበት ወላጅ ብቻ ነው ።በቃ እነሱ እንደ እንቁላል ተጠንቅቀው ያሳደጓቸው የወላጆቻቸው ምርጦች ናቸው ። እነሱም የወላጆቻቸው ትምክህት ተጋብቶባቸው ነው መሰል ። በኑሮ እና እነሱ ባወጡት መስፈርት ደረጃቸው ካልመሰላቸው ሰው ጋር መገናኘት አይፈልጉም ። ሰመረ የጠይም ቆንጆ ቁመናው ያማረ ፈገግ ሲል ጥርሶቹ እንደፍሎረሰንት አንቦል ወገግ የሚሉ ቀኑን ሙሉ አብሬው በዋልኩ የሚያስብል የሃያ አመት ወጣት ነው ። የስህል ችሎታም ስላለው ትምህርቱንም የሚማረው በዚያው ዙሪያ ነው ምንም እንኳ ቤተሰቦቹ ቢዝነስ እንዲያጠና ቢፈልጉም ።
ሌላው ጌታ ሁን ነው _ጌታሁን ከ ሰመረ አጠር ያለ እና ድንቡሽቡሽ ያለ ወጣት ነው ትንሽ ከተናደደ ቀይ ፊቱ ቲማቲም ነው የሚመስለው ኩርፊያውን መደበቅ አይችልም ። ትምህርቱን መደበኛውን እንደጨረሰ ነው ያቆመው ። 'ያው ተምሬ ገንዘብ ለማግኘት ነው አይደል በቃ እኔ እንደው ለዚ መልፋት አይጠበቅብኝም ይልቅ እናቴን ድርጅቷ ውስጥ ያለባትን ጫና ላግዛት ይገባል ለእውቀቱ ከሆነ መፀሐፍ አነባለው ' ብሎ ለጠየቀው ሁሉ መልስ ሰጥቶ አፍ አዘግቷል ።
ሦስተኛው እንየው ነው እንየው ከሰመረ ጋር በቁመት እኩል ነው የቀይ ዳማ መልክ ያለው ሲሆን መልከመልካም የሚባል አይነት ነው በጣም ችኩል እና ተለዋዋጭ ስሜት አለው ። ለዚህም ይመስላል መደበኛ ትምህርቱን ከጨረሰ በዋላ የተለያየ ትምህርት እየጀመረ የሚያቆመው ። በቅርቡ ደሞ ሞዴሊንግ እየሰለጠነ ነው ። የመጀመሪያው ቀን ለሰመረ ሲነግረው ። የሚያማምሩ ጥርሶቹን መክደን አልቻለም እረጅም ሳቅ ነበር የሳቀው ።
እንግዲ እነዚ ወጣቶች የከተማችን ቱጃር ልጆች ናቸው ። የፈለጉበት ሄደው በነፃነት መዝናናት በነፃነት የፈፈለጉትን ማድረግ የለመዱ ። ጮክብለው የሚያወሩ ጮክ ብለው የሚስቁ የከተማው ገዢ የሚመስሉ ። የፈለጓትን ሴት ነይ ሂጂ ማለት የለመዱ ። ሴቶቹላይ ያደረጉትን የሚይደባበቁ ። በምስኪን ሴቶች የሚሳለቁ የሚያደርጉት ነገር ሌላው ላይ ምን እንደሚያስከትል እንኳ ለማሰብ ጊዜ የሌላቸው ። አንዳንዴ ሰመረ ነገሮችን ለማስተዋል ቢሞክር እንኳ ዳግም ተጎትቶ በነሱ ስር መከተቱ አይቀርም
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19