✨✨✨በ'ነሱ ቤት✨✨✨
✨✨✨ክፍል ሦስት✨✨✨
አብላካት ቀጫጭን ጠይም እጆቿን በብስጭት እያወናጨፈች ሰመረን ተቃወመች ጮክብሎ መናገር አይሆንላትም እንደዛ ካደረገች እንኳ ዕንባዋ ይቀድማታል እንደዛ እንዲሆን ደሞ አልፈለገችም በማንም ሰው ፊት እንደ ዕፃን ማልቀስን አትሻም ስታለቅስ የኖረችባቸው ጊዜያቶች እንዲያበቁ ብቻ ነው አሁን ላይ የምትፈልገው ። ከዚበፊት ስለ እናቷ መጠቀት አልቅሳለች ስለችግራቸው አልቅሳለች እንደሌሎች ልጆች የፈለገችውን ማግኘት እንደማትችል ባወቀች ጊዜ አልቅሳለች ። እርቧት የምትበላው ነገር በቤትውስጥ በማጣቷ አልቅሳለች ። ዛሬላይ ግን ሁሉ ነገር እንዲያበቃ ነው የምትፈልገው የወጣት አሮጊት የመሰለችባትን እናቷን ከችግር ማውጣት ያን ባትችል እንኳ ልታግዛት ፈልጋለች ፡ ለዚህም ነው በፌስቡክ ብቻ ካወቀችው ጥሩ ሰው ከመሰላት ሰው ጋር ቀጠሮ የያዘችው እናም ያሰው ብዙ ነገር ነው ቃል የገባላት ስራ እንደሚያስቀጥራት ሕይወቷ እንደሚቀየር የተሻለ ኑሮ እንደሚኖራት ጭንቅላቷን የሞላት ፡እናም ጓጉታ ነበር ይሄ የተረገመ ጫማ ሊያሰናክላት ነው በዛላይ ሰመረ ጫማዋን እየወረወረ አበሳጫት ።
አስተናጋጁ ሰሚር የልጅቷን ጫማ እየወረወረ በሚስቀው ሰመረ ላይ ከምር ተናደደበት ግን ንዴቱ ዋጥ አድርጎ ወደ እሬስቶራንቱ ከመመለስ ውጪ ምንም ማድረግ አልቻለም ።
ሰመረ ጫማዎቿን ለማምጣት የምትሯሯጠውን አብላካትን እጇን ይዞ በቁጣ አስቆማት ።አብላካት ጭራሽ ከሱም ብሶ ሲቆጣት ትላልቅ የሚያምሩ አይኖቿን አፍጣ በመገረም ታየው ጀመር ።
"ስሚ ሚጣ ከአሁን በዋላ ያጫማ አብቅቶለታል የምን ችክ ማለት ነው ።በቃ ሌላ ጫማ ሄደሽ ግዢ አለበለዚያ በጥፊ ነው የምልሽ እሺ"አላት ፊቱን እንዳኮሳተረ ።አብላካት ተገርማ
"ጭራሽ እንዴ ለምንድነው እንዲ የምታደርገው?"አለች ሰመረ እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ ብዙ የመቶብር ኖቶች ሲያወጣ አፋን ከፍታ ቀረች
"ለምን ምናምን ማለትሽን ትተሽ እንኪ ውሰጂና የምትፈልጊውን ጫማ ግዢ ለጊዜው የያዝኩት ይሄንን ነው የማይበቃሽ ከሆነ ነገ እዚው ስላለው መጥተሽ ውሰጂ ይሄን ጫማግን ደግመሽ እንዳታይው ሲያስጠላ "አለ ፊቱን አጨፍግጎ
"ግን ለምንድነው ይሄንን የምታደርግልኝ "አለች ድጋሚ
"ይኽውልሽ አጉል ክርክርሽን ተዪ ጫማው ተበላሽቶብሻል እኔ ደሞ ስላለኝ ነው የምትገዢበት የሰጠውሽ አሁን ሂጂ"አላት እጇላይ ያስቀመጠላት ብር ቡዙነው ለሷ እምቢ እንዳትል ችግሯን አሰበች እሺም እንዳትል ሒሉንታ ያዛት
"አንቺ ሚጣ ለምንድነው ሄደሽ የማትገዢው ያው እዛ ከኮስሞ አጠገብ የሴቶች ጫማ መሸጫ ይታየኛል እዛ ሄደሽ ግዢና ከዚ አካባቢ ሂጂ "አለ ሰመረ
"ግን እኮ ጫማው የሰው ነው ማለቴ ጓደኛዬ አንድ ሰው ስራ ሊያስገባኝ ነው እና ጫማሽን አውሺኝ ብዬ ለምኛት ነው የሰጠችኝ ።እና እሷ እራሱ የታላቅ እህቷ ነው ጫማውን ወስጄ አሰርቼ ካልሰጠዋት ትጣላኛለች ።"አለችው ፈራ ተባ እያለች ።ሰመረ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨነቀ ።እንዴ ምን አይነት ነገር ነው አሁን ይሄም ጫማ ሆኖ ይዋዋሱታል ።አለ
"እሺ እንደፈለግሽ አድርጊ ሚጣ "አላት አዘን ብሎ
"ስሜ አብ ላካት ነው "አለች እና ስልኳ ሲጮኽ ሰምታ ከያዘቻት ትንሽዬ ያረጀች ቦርሳ ውስጥ ስልኳን አውጥታ "ሄሎ ሰላም ዋልክ ።አዎ አዎ ይቅርታ ግን አሁን መጥቻለው ።ትንሽ ጠብቀኝ ችግር ገጥሞኝ ነው እኮ ።አይ አይ አሁን ይሻላል ። እኮ ማማታማ እናቴ አትፈቅድልኝም ። እባክህ እንደዛ ማለቴ አይደለም ።እኔ ስራውን እፈልገዋለው ። እባክህ ቆይ አትዝጋው እኔ እኮ ማታ መውጣት ስለማልችል ነው ። ግን እኮ ስራው ያስፈልገኛል እናቴን መርዳት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ ።እሷ እየተጎዳችብኝ ነው እባክህ ።ቆቆይ አትዝጋው ,,,,"ስልኩ ጆሮዋላይ ተዘጋ አብላካት የምትፈራው ዕንባዋ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ ።አጠገቧ ሰመረ መኖሩን እንኳ እረስታለች ,,,,,,,,,,
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19