✨✨✨በ'ነሱ ቤት✨✨✨
✨✨✨ክፍል አራት✨✨✨
ሰመረ እንደዚ አይነት መጨናነቅ የለመደ ልጅ አይደለም እና ሁኔታዋን አይቶ'ምነው እቺን ልጅ ላናድድ ብዬ ከተቀመጥኩበት ባልተነሳው በገዛ እጄ አባባይ ልሁን እኔ ሲጀመር ምን አገባኝ !ማድረግ ያለብኝን አድርጌላታለው በቃ የራሷ ጉዳይ 'ብሎ ትቷት ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ ። ጓደኞቹ ገና ከመምጣቱ በተረብ አላስቀምጥ አሉት።
"እኔ የምልህ ከዚች አመዳም ጋር የዚን ያክል ክርክሩ ምንድነው ?ደሞ አይደብርህም እንዴ ያንን አስቀያሚ ጫማዋን ከእጇ እየነጠክ ትወረውራለህ ሃሃሃ በል በል አሁን ሂድና እጅህን ታጠብ ሆሆሆ ሳም ሙት! አንዳንዴ ምንም አትገባኝም በላይህ ላይ ጀርም ትጋብዛለህ ሃሃሃሃ"ብሎ ጌታነህ ሳቀበት ።እንየው ቀበል አድርጎ "እኔ እኮ የገረመኝ ገንዘብ አውጥተህ መስጠትህ ምን ፈልገህ ነው ግን ኪኪኪ ለነገሩ አጥበህ አስቆንጅተህ በትበላው የሚያስከፋ አይደለም በደንብ ከተያዘች ቆንጆ ነገር ናት ግን ጓደኞቼ እየወረዳቹ ነው ዛሬ 😀ወይ ከዚ በረንዳ ወደውስጥ እንግባ 😀"አለ ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ።
ሰመረ እነሱ የተናገሩት ነገር ምኑም ደስአላለውም ይብስ ተከፋ ሁለቱም ባሰቡት መንገድ እንዳላሰበ ደጋግሞ አስረዳ ። ከነሱ ጋር ክርክሩ አላዋጣ ሲለው አይኖቹን መልሶ ወደ መንገዱ ወርወር አደረገ አብላካት እየተወለጋገደች ሁለቱን ጫማወቿን አንጠልጥላ በተስፋመቁረጥ ስትራመድ አያት ለምን እንደው ያላወቀው ስሜት ወረረው ልቡ አዘነ ይህቺ ልጅ ገና ታዳጊ ናት ለምንድነው የዚን ያክል መከፋት ያለባት ምን አይነት የተቸገረ ቤተሰብ ቢያሳድጋት ነው እንዲ የሆነችው አለ ለራሱ ፣ሰው በዚመጠን ደሃ ይሆናል ጫማ እስከመዋዋስ ለዛውም ጀየሚያስጠላ ጫማ ይገርማል ። በመንገዱላይ ብዙ ሰው አይታይም አብላካት ያመንገድ አላልቅ ያላት ይመስላል በራሷ በጣም ተሸማቃለች ገና ከሳምንት ጀምሮ ስትዘጋጅበት የነበረ ቀጠሮ ነው የተበላሸባት ለሷ የመጀመሪያ ቀጠሮዋ ነው ለዛውም ከችግር የምትወጣበት ቀጠሮ ነገር ግን በገዛ እጇ አበላሸችው ምነው ታምራትን ከማስከፋው የራሴን ጫማ አድርጌ በመጣው ይሄኔ እኮ አግኝቼው የምሰራበትን ቦታ አሳይቶኝ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ እመለስ ነበር የተረገመ ጫማ ።ደሞስ ምን አጣደፈኝ ቀስ ብዬ አልሻገርም ነበር ።በራሴው ስህተት ነው ስራውን ያጣውት ።ዕድ ለቢስ ነኝ ሲጀመር ብላ ስንጥቅ የበዛባትን የሞባይል ስልኳን አየች በተስፋ ታምራት የተባለው የፌስቡክ ጓደኛዋ ይደውል ይሆናል በሚል ምኞት ።ይህችን የሞባይል ስልክ ከሰው ላይ የገዛችላት እናቷ ነች ከዘጠኝ ወደ አስር በጥሩ ውጤት ስላለፈችላት ደስታዋንና በሷ መኩራቷን ለማሳየት ።እና አብላካት የዛንቀን ከጓደኞቿ እኩል ሞባይል በመያዟ ደስታዋ ወደር አልነበረውም። ከዛን ጊዜጀምሮ ፌስቡክ ከፍታ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ታወራለች ከአንገት በላይ ተነስታ የምትለቃቸው ፎቶዎቿ የሚስቡ በመሆናቸው ብዙ ወንዶች ኢንቦክስ እየገቡ ያወሯታል የፍቅርጥያቄ ያቀርቡላታል አብላካት ለሁሉም በየዋህነት ገና ለዛ እንዳልደረሰች ትፅፍላቸዋለች ።ብዙዎቹ ያለምጡባታል ።ከነዛ ውስጥ ግን የታምራት አቀራረብ ይመቻታል ልጅነቷን ስትነግረው መገመቱን እና እሱ እህት እንዳለው ልክ በሷ ዕድሜ መሆኗን እየነገረ አግባባት ከዛ በዋላ ስለቤተሰብ ስለትምህርት እየጠየቀ ችግሯን ሁሉ ሳትደብቅእንድትነግረው አደረገ ከዛም ነገረችው ።እናቷ እሷን በልጅነቷ ሰውቤት ሰራተኛ ሆና ከአሰሪዋ ልጅ እንዳረገዘቻትና አሰሪዎቿ ይሄንን ሲያውቁ እንዳባረሯት ከዛም እሷን ጎዳናላይ እንደወለደቻት ከዛ በዋላም እናቷ እጅ ሳትሰጥ ጉሊት እየሰራች ፍራፍሬ አትክልት እየሸጠች እንዳሳደገቻት አወራችው ።በጣም የሚያሳዝን ታሪክ እንዳላት እና እሷን ለመርዳት ሲል የአክስቱን ልጅ እንደሚያናግራት እና እሷ ፑቲክ ውስጥ እንደሚያስቀጥራት ነገራት ።ይሄንን ያላት ቀን በደስታ ነበር የሰከረችው ። በተለይ እናቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እግሬን እየወጋኝ ነው እያለች ከምትሰራበት ጉሊት መመለሷ እየተለመደ መጥቷል እመም ይሰማታል ይሄን ስለምታውቅ ።እሱ ስለስራ ሲያወራት ቀጥታ የታያት እናቷን ማገዟ ነው ።አብላካት ስላረፈድሽ የማልቀርበት ጉዳይ ስላለኝ ሄጃለው ባይሆን ማታ ተገናኝተን ተጫውተሽ ትመለሻለ ሲላት አይመቸኝም ስትለው ድንገት ቅይር ብሎ ካልሆነ ይቅርብሻ ነበር ያላት በጣም ተናዳለች በፌስቡክ እንዳወራት አልሆነላትም ።ሰው በአንድጊዜ ጥፋት እንዲ ይለወጣል ያሳዝናል ።'ወይኔ እናቴ መቼ ልደርስልሽ ነው 'እያለች በአዘን ተቆራምታ በባዶእግሯ ትጓዛለች ። ሰመረ የሰጣትን ብር ጨምቃ ይዛታለች ።
*ሰመረ ተነስቶ ቆመ ጓደኞቹ እኩል ወዴት ነው አሉት መጣው ብሎ በረንዳውን በፍጥነት መውረድ ጀመረ
ጓደኞቹ ግራ በመጋባት ተያዩ ሰመረወደ አብላካት አቅጣጫ ፈጠነ,,,,,,,
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19