ካልሰማችሁ "Data is the future currency"። ሀገራት ከጊዜያት በኋላ የሚወዳደሩትም የሚገዳደሩትም ባላቸው dataset ይሆናል ማለት ነው። ለዚህም ሲባል ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸው ትላልቅ ሀገራት የራሳቸውን " Data monopoly" ለመፍጠር የሚታገሉት።
ቻይና መሰረቱ አሜሪካ የሆነውን ፌስቡክ መጠቀም አትፈልግም ምክንያቱም ቻይናውያን ፌስቡክ ተጠቀሙ ማለት አሜሪካ በቻይና ፖለቲካም ሆነ ኢኮኖሚ ላይ አሻጥር መስራት ብትፈልግ የተጠቃሚዎችን interest በደንብ ስለምታውቅ ጉዳዩ ውሃ የመጠጣት ያክል ቀላል ነው። ለእውነት የቀረበ የውሸት ዜና አቀነባብራ የቻይናውያንን ሀሳብ ማስቀየር ቻለች ማለት ነው።
ሌላው እነዚህ giant tech companies ትልቅ ኢኮኖሚ ያንቀሳቅሳሉ። ፌስቡክና ዩቲውብ ይከፍላል አይደል? (እኛን ሽጦ እኮ ነው 😃)
እነዚህ የሶሻል ሚድያ ፕላትፎርሞች የተጠቃሚዎችን ፍላጎት በየጊዜው ያጠናሉ። ምን እንደምንጠላ ምን እንደምንወድ ያውቃሉ።
ስለዚህ የኛን ፍላጎት ፍላጎታችን. ለሚፈልጉ በመሸጥ ሀብት ያካብታሉ። ለድሆች የሚሆን ምርትን መሸጥ ለፈለገ ድሆችን መርጦ ማሳየት፣ ለሴቶች መሸጥ ለሚፈልግ ሴቶችን ብቻ መስጠት ለነ ፌስቡክም ሆነ ቲክቶክ ቀላል ነው።
የሶሻል ሚድያዎች ስራ የማንኛውንም ግለሰብ አካውንት በደንብ በማጥናት የግለሰቡን ኮፒ ሰርቨራቸው ላይ መፍጠር ነው። ለምሳሌ የኔን ኮፒ መፍጠር ሲፈልጉ የምወደውን ምግብ፣ ሰው፣ የማየውን የፊልም አይነት፣ የሚመቸኝን የሰው ባህሪ፣ ጫማ፣ ልብስ እያለ ሁሉንም ነገሬን ከምሰጠው data እና ፕላትፎርሙ ላይ ባለኝ እንቅስቃሴ በመረዳት ጠንቅቀው ለመረዳት ይሞክራሉ። ያገኙትን ዳታ አቀነባብረው ስለኔ ያላቸውን መረዳት ያሻሽላሉ።
ቲክቶክ ተጠቃሚን በመረዳት ረገድ ከሌሎቹ የተሻለ algorithm አለው። ይህ ደግሞ ቻይናን የዳታ ባለሀብት የማድረግ ትልቅ አቅም አለው ማለት ነው። አሜሪካ በነ ጎግልና ፌስቡክ ስታደርገው የነበረውን ነገር ቻይና በቲክቶክ አሻሽላ ስትመጣ ስጋት አድሮባታል። ቲክቶክ የአሜሪካውያንን ዳታ ያስቀመጥኩት እዛው አሜሪካ ቴክሳስ ነው ቢልም የሰርቨሩ back up ግን ሲንጋፖር መሆኑ ጋር ተደማምሮ ቲክቶክ ለአሜሪካ ስጋት ሆኖባታል።
Tiktok በአሜሪካ ባለፈው አመት(2024) ብቻ 12.34 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል። በአንጻሩ ፌስቡክ በቻይና የተዘጋው 2009 ላይ ነበር። ሜታ በሌሎች ፕላትፎርሞቹ በ2013.49 ቢሊዮን ዶላር ማትረፍ ችሎ ነበር (businesses insider)
ድጂታላይዜሽን ከተለመደው የሀገራት import/export እና ሚሊተሪ አቅም ባለፈ ሌላ መለካኪያ አምጥቷል እላችኋለሁ