#ለሰኞ
#backtowork
ሁሉም ቀን እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ህይወት ትቀጥላለችና ነገን በማሰብ እንቀጥላለን ። ከአምስት አመታት በፊት ወደ custor computing PLC ተቀጥሬ ስገባ በዋናነት አለኝ የምለው ብቃት ቶሎ የመማር በፍጥነት deliver ማድረግ የመጀመር ብቃት ነው። የመጀመሪያ ልጃችን ተረግዞ ስለነበር የሚጠብቀኝ ነገር ብዙ እንደሆነ ስለተረዳሁ በአድሱ መስሪያ ቤት የምንገለገልባቸውን tech stacks ቀን ሌሊት ፣ ቅዳሜ እሁድ ሳልል መቀጥቀጥ ጀመርኩ። በተለ Maru Abebe ያኔ በ97$ የገዛልኝን አንድ መጽሀፍ ጨምሮ አንድ ሙሉ angular course ወስጀ በዛውም የተሰጡኝን ስራዎች ለመከወን እተጋለሁ።
እዛ መስሪያ ቤት ከመግባቴ በፊት freelancer ሆኘ fiveer ላይ ጥሩ rating ስለነበረኝ ስራዎችም ይመጡልኝ ነበር። (ስራ ላይ ስራ ሊደረብብኝ 😊)
በእሁዱ ቀን 65$ ዋጋ ያለው ስራ ድንገት ታዘዝኩና ይሄንማ አልመልሰውም ብዬ ባለቤቴን እናቷ ጋር ሸኝቸ ወደ ቢሮ መሄድ። ሙሉ ቀኔን ሰውቸ የመቶ ብር ኢንተርኔት ፓኬጅ ሞልቸ ሙሉ ቀን ታግዬ ሰርቸ ተረከበኝ ስለው ጣጣ አበዛብኝ፣ መጀመሪያ ያልተነጋገርነውን ሁሉ መጨመረ ጀመረ። እኔም ጨማምሬለት ምሽት አንድ ሰዓት ሲሆን ሌላም የቀረ ነገር አለ ብሎ ኮንትራቱን ሰረዘው 🤔
የሙሉ ቀን ልፋቴን ውሃ ቸልሶበት መቶ ብሬንና ጊዜየን አቃጥሎ ምንም አሳማኝ ባልሆነ ነገር ኮንትራቱንሰርዞብኝ ብናደድም አልሃምዱሊላህ ብዬ በምሽት ወደ ቤቴ ተመለስኩ።
Sometimes we earn, sometimes we learn
መልካም የስራ ሳምንት