የበግና ኮርማ አይደለም መስዕዋቱ
የተከፈለለት ለበዛው ሀጥያቱ
የኢየሱስ ደም ነው የሰጠኝ ህይወትን
ከአብ ያስታረቀኝ ከቶ ያላሰብኩትን
በብቸኛ ልጁ በቃ አለኝ በሚለው
የአለምን ሀጥያት ከምንጩ ከደነው
አምላክ ሆኖ ሳለ የሚችል ሁሉን
ተሸፍኖ ጥፊን ግፍ መከራውን
እነዛ ሚስማሮች ከቶ አልሳሱለት
የሰው ልጅ ጭካኔ እጅጉን በዛበት
ትንቢቱ እንዲፈፀም እንዲሆን ግድ ነው
የአለምን ሀጥያት የደሙ ሀይል ሻረው
— ኢሳይያስ 53፥5
የተከፈለለት ለበዛው ሀጥያቱ
የኢየሱስ ደም ነው የሰጠኝ ህይወትን
ከአብ ያስታረቀኝ ከቶ ያላሰብኩትን
በብቸኛ ልጁ በቃ አለኝ በሚለው
የአለምን ሀጥያት ከምንጩ ከደነው
አምላክ ሆኖ ሳለ የሚችል ሁሉን
ተሸፍኖ ጥፊን ግፍ መከራውን
እነዛ ሚስማሮች ከቶ አልሳሱለት
የሰው ልጅ ጭካኔ እጅጉን በዛበት
ትንቢቱ እንዲፈፀም እንዲሆን ግድ ነው
የአለምን ሀጥያት የደሙ ሀይል ሻረው
“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5