Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
⚠️Somalia
ሶማሊያ በመማሪያ መፅሀፍቷ የኢትዮጵያን መሬት ወደ ራሷ አካተተች
ሶማልያ በመማሪያ መፅሐፍቶቿ ላይ የኢትዮጵያን ግዛቶች በራሷ ግዛት ስር ማካተቷ ተሰማ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ‹የሕልውና ስጋቴ ናት› በማለት በመማሪያ መፀሰሐፍቷ ላይ አስፍራ ተማሪዎቿን እያስተማረች ነው፡፡ ለዚህም የመማሪያ መፅሕፍቷን እንደገና መከለሷን ኢንሳይድ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
የሶማልያ መንግስት ሶማልያውያን ታዳጊዎች እና ህፃናት ኢትዮጵያ የህልውና ስጋት እና የሶማሊያ ታሪካዊ ጠላት እንደሆነች እንዲያምኑ በትምህርት ቤት ልጆች ላይ ማስረፅ ጀምሯል። ይህንን ትርክት ለመደገፍ የሞቃዲሾ አስተዳደር ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የታሪክ እና የጂኦግራፊ መማሪያ መፅህፍትን ከልሷል፡፡
እነዚህ የተሻሻሉት የታሪክ መማሪያ መፅሃፍት በኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሀል ጥላቻ እና ቁርሾን የሚፈጥሩ ምእራፎች የተካተቱበት ነው፡፡ በተጨማሪም የተሻሻለው የጂኦግራፊ መማሪያ መፅህፍት የኢትዮጵያን መሬት በሶማሊያ ግዛት ውስጥ እንዲካተት እና እንዲጠቀለል አድርጎ ነው ያሻሻለው፡፡ በሶማልያ ግዛት ስር እንዲካተት የተደረገው የኢትዮጵያ መሬት አብዛኛው የሶማሌ ክልል ክፍል ነው፡፡
ይህም የሶማልያ ታዳጊ ትውልድ የዚያድ ባሬ ‹የታላቋ ሶማልያ› ትርክት በውስጣቸው ለማስረጽ ታልሞ የተደረገ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
Via Brook News