በቅርቡ አገልግሎት ለሚጀምረው የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት የሚያገለግል የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት ተካሄደ
=================================================================
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2017 ዓ.ም:- በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ለሚጀምረው የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት የሚያገለግል የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአት (Digital Certificate Key Ceremony) ተካሄደ፡፡ ሥነ ሥርአቱ የተከናወነው የብሔራዊ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን ሆኖ በሚያገለግለው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ነው፡፡
የዲጂታል ሰርተፊኬት ይፋዊ ቁልፍ የማመንጨት ሥነ ሥርአቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገግሎት በቅንጅት ያከናወኑት ሲሆን፤ በመርሃ ግብሩ ላይም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊትን ጨምሮ፤ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ጎሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ተገኝተዋል፡፡
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA