Buna Tech ቡና ቴክ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


Welcome to our Buna Technology Telegram channel
It's a channel where you find the amazing and new things about Computer and technology that you don't know in photo and writing, you get a variety of funny surprises and you get knowledge. Thanks 🙏

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций


በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሮቦቶች የግማሽ ማራቶን ሩጫ ላይ ተሳተፉ።

በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በሚሳተፉበት Yizhuang በተሰኘ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ላይ ከ20 በላይ ሮቦቶች መሳተፋቸው ተገለፀ።

ውድድሩ ላይ የተሳተፉት ሮቦቶች እንደ DroidUP እና Noetix Robotics ባሉ ዝነኛ የቻይና ድርጅቶች የተሰሩ ሲሆኑ ውድድሩ ላይም ትላልቅ እና መለስተኛ ሮቦቶች ሲሮጡ ተስተውሏል።

የ21 ኪ.ሜ አልያም 13 ማይል ገደማ ሩጫ ከተወዳደሩት ሮቦቶች መካከል ጫማ ለብሰው መወዳራቸው እና አንዳንዶቹ ገና ከመጀመራቸው መውደቃቸው ትኩረት ከሳቡ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።

አሸናፊውም ከBeijing Innovation Center of Human Robotics የመጣው Tiangong Ultra የተሰኘው ሮቦት ነው። ውድድሩን ለማጠናቀቅም 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ የፈጀበት ሲሆን በአንፃሩ ከሰዎች ተዎዳዳሪዎች አንደኛ የወጣው 1 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀበት።

ውድድሩን ትታዘቡ ዘንድ በሁለተኛው ቻናላችን አጭር ቪድዮ አስቀምጠንላችኋል። click here


Репост из: Buna Digital Marketing
🚨 LAST CHANCE to Submit Your Paper for ETEX 2025!
Deadline Extended to Friday, 25th April
Are you a tech researcher, academic, or innovator? Present at Ethiopia’s leading tech expo and share your work on:
* Cybersecurity in the AI Era
* Smart Cities
* Fintech
* Trustworthy AI
* Quantum Computing

📄 Submit 10+ page papers (PDF + LaTeX, IEEE format)
📧 Email: Seble.hailu@insa.gov.et
🏅 Top papers get special recognition!
📢 Acceptance Notification by 5th May

Explore sponsorship and exhibition opportunities: https://bit.ly/3G3lPwc
Stay updated – Join our Telegram channel: t.me/ETEX_Ethiopia

#ETEX #ETEX2025 #DigitalEthiopia #TechForAfrica #Innovation
#EthiopiaTech #digitaltransformation

Ethiopian Artificial Intelligence Institute| Information Network Security Administration| Cyber Security Council | QNA Marcom | African Union


Facebook የሁሉንም ሰው friend list ሙሉ በሙሉ Delete አድርጎ እንደ አዲስ ሊጀምር እንደሚችል ታወቀ።

የአሜሪካ ፌደራል ንግድ ኮሚሽን የMeta ስራ አስፈፃሚዎች ከ2022 ጀምሮ የተለዋወጧቸውን የተለያዩ ኢሜሎች ይፋ አድርጓል። በዚህ የኢሜል ልውውጥ የFacebook መስራች Mark Zuckerberg ቀስ በቀስ የFacebook ተወዳጅነት እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ ለስራ አስፈፃሚዎቹ ፅፎላቸዋል።

ለዚህም ምክንያቱ ዘመኑን የተከተለ user interface እና አዳዲስ የማህበራዊ ሚዲያ አሰራር አለመኖሩ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ለዚህም አንዳንድ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ከነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ አንዱ "potentially crazy idea" ሲል የገለፀው የሁሉንም ሰው Facebook friends ዜሮ በማድረግ በአዲስ አሰራር ሊተካው እንደሚችል ተናግሯል።

ይህም እንዲሆን ያሰበበትን ምክንያት ሲያብራራ በአሁን ዘመን ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ከ1 ለ 1 ጓደኝነት ይልቅ ለተከታይነት የበለጠ ትኩረት እየሰጡ ስለሆነ ነው ብሏል።

ስለዚህ ቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠቀሙትን የfollowing አሰራር ሊከተሉ እንደሚችሉ ይፋ በተደረገው ኢሜል ላይ አብራርቶላቸዋል።

Zuckerberg ቃል በቃል "Facebook’s friend system is outdated. Maybe we should blow it up and start fresh — more like other modern apps." በማለት ሲፅፍ ሊወስዳቸው የሚችላቸውን ዘርዝሯል።
⚫Deleting everyone’s friend lists
⚫Letting users rebuild their connections from scratch
⚫Possibly shifting from friending to a following-based system (like Instagram or Twitter)

ይህ እርምጃ በጣም risk ያለው ስለሆነ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት በትንንሽ ሃገሮች ላይ ለመሞከር እንዳሰበም ሃሳቡን ሰጧል።

💬ለውጡን እንዴት አያችሁት? Facebook ላይስ ስንት ጓደኞች አሏችሁ?


Репост из: Buna Digital Marketing
እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለዉን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፈራ ኑና እዩ።
ማቴዎስ 28÷5

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የመተሳሰብ ይሁልን።
ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላምን ያድርግልን።🙏🙏


Репост из: Buna Digital Marketing
📢Exciting 2017 E.C. Summer STEM Opportunity!

The Ministry of Higher Education, in collaboration with Ethiopian universities and a global STEM organization, is launching a prestigious 2-month summer program for 700 outstanding students across Ethiopia.
🔹 Transportation: All transport costs covered by STEM program
🔹 Location: Selected universities
🔹 Eligibility: Grade 9–12 students
🔹 Benefits: Hands-on STEM experience, international certificates, and professional networking
🔹 Special Feature: Learn from international experts, including STEM professionals and educators from NASA!

🎓Special Scholarship Opportunity!
Out of the 700, 50 will earn scholarships to continue their studies at top universities in the USA and Europe.🚀

Led by STEM manager Prof. Yenealem, this program shows Ethiopia’s commitment to developing future science and tech leaders.

🗓 Deadline: April 25, 2025
📌Apply now:https://forms.gle/sBFNvw6Ha7rDhC7W7

Don't miss this incredible opportunity!
#MinistryOfEducation #STEM #TikvahEthiopia #NASA


Google prompt engineering.pdf
8.3Мб
በሚመጡት ጥቂት አመታት ውስጥ አዲስ ከሚመጡ የስራ ዘርፎች ውስጥ prompt engineering አንዱ ነው።

እያንዳንዱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተጠየቀውን ጥያቄ የሚመልሰው እኛ በምናስገባለት ፅሁፍ ላይ የተወሰነ ነው። ስለዚህ Prompt engineering ማለት አንድ AI Large Language Model (LLM) የተሻለ ውጤት እንዲሰጥ ምን አይነት ጥያቄ እናስገባ የሚለውን የምናጠናበት ዘርፍ ነው።

አለማችን በAI LLM እየተጥለቀለቀችበት ባለችበት በዚህ ዘመን ይህ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ መጥቷል።
ሰሞኑን Google በPrompt engineering ላይ ትኩረት የሚያደርግ ባለ 69 ገፅ ዶክመንት ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህ ዶክመንት መሰረታዊ የPrompt engineering መረጃዎችን ይዟል።

ዶክመንቱን ከላይ አያይዘንላችኋል።


Zero-day exploit ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ምን ማለት ይመስላችኋል?

Internet ላይ search ሳታደርጉ እስኪ የምታስቡትን comment ላይ ፃፉ።


Репост из: Buna Digital Marketing
✨ "People have their own problems, and you have yours, so you don’t have to tell the world about every single issue that you have because nobody cares. 🤷‍♂️ The same can be said about you; if somebody tries to get you involved in his or her personal drama, you wouldn’t care, right?" - Dara Ly ✨


ጎረቤታችን ሶማሊያ ለSTARLINK የስራ ፈቃድ ሰጠች።

የሶማሊያ ብሄራዊ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ስታርሊንክን በመላ ሀገሪቱ የሳተላይት የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በይፋ ፍቃድ ሰጥቷል።

በሞቃዲሾ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ የስታርሊንክ ተወካዮች አገልግሎቱ በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፣ ይህም ከከተማ ርቀው በሚገኙ ገጠራማ የሀገሪቱን ክልሎች የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስፋት ይረዳል።

ምንጭ: Bloomberg


እኛ ሀገር የሚጀመር ይመስላችኋል? 😋


GROK AI playstore ላይ launch ተደርጓል።
Download አድርጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።

Play strore link
https://play.google.com/store/apps/details?id=ai.x.grok


Репост из: Biruk Afework
“አያትየው ስድስት ወንድና ሶስት ሴት ልጆች አሏት፤ ነገር ግን አብልጣ የምትወደው እስር ቤት ያለው ሰካራም ልጇን ነው” 🤗

                    ―ቼክሆቭ
           Secret notebook📖


የውድድር ዕድል ጥቆማ

በኤ.አይ እና ሮቦቲክስ ዙሪያ Presidential African Youth in AI and Robotics Competition የተሰኘ አፍሪካዊ ውድድር ተሰናድቷል።

በ12 ዘርፎች የሚደረገው ውድድር እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ለሆኑ አፍሪካውያን ወጣቶች ብቻ የቀረበ ሲሆን አሸናፊዎች የሚጋሩት 120 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

ለውድድር የሚሆን ስራ ለማቅረብ እስከ ጁን 13፤2025 ድረስ እንደሚቻል በውድድሩ ድረ-ገፅ ተገልጿል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ በዘርፉ ልምድን ያካበቱ አፍሪካዊያን የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ጥሪ እየተደረገ ይገኛል።

Presidential African Youth in AI and Robotics Competition እ.ኤ.አ በ2024 ጅማሮውን ያደረገና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሁነት ነው።

የዘንድሮው ውድድር በአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ፣ በደቡብ አፍሪካ መንግሥት እና ኤሊቬት ኤ.አይ አፍሪካ ትብብር የተዘጋጀ ነው።

ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የመወዳደሪያ መስፈርቶችን እንዲመለከቱ እና በውድድሩ እንዲሳተፉ እንጋብዝዎታለን።
https://ele-vate.co.za/african-youth-in-artificial-intelligence-and-robotics


Репост из: የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
የጥንቃቄ መልዕክት ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች❗️

የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ አድራሻዎች ለሀገራችን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በይበልጥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አካዉንቶችን በመንጠቅን ከፍተኛ ስጋት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አረጋግጧል። ከተለያዩ አካላት በቴሌግራም የሚደርሱን ሊንኮች በርካታ አደጋዎችን የሚይዙ ሲሆን የሚከተሉት አደጋዎች በዋናነት ይገኙበታል፡

👉የግል መረጃ መጠለፍ:- እንደ የባንክ መለያ ወይም የይለፍ ቃል ያሉ መረጃዎችን መሰረቅ፤

👉የማልዌር ስርጭት:- ስልኮችን ወይም ኮምፒውተሮችን የሚጎዱ ቫይረሶች፤

👉ማጭበርበሪያ:- ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ ተስፋዎች (እንደ ውርርድ ወይም ኢንቨስትመንት) መታለል፤

በመሆኑም ማኅበረሰቡ በቴሌግራም አማካኝነት የሚላኩለትን አጠራጣሪ ሊንኮች ከመክፈት እንዲቆጠብ እያሳሰብን፤ ሰሞኑን በቴሌግራም ከሚላኩና በፍጹም ልንከፍታቸዉ ከማይገቡ ሊንኮች መካከል የሚከተሉት ከታች በምስሉ ያሰፈርናቸዉ ይገኙበታል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቴሌግራማችን አጠራጣሪ የሆኑ ሊንኮች ካጋጠመን ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሚከተሉት አድራሻዎች ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
• e-mail: ethiocert@insa.gov.et
• ነጻ የስልክ መስመር፡ 933


Breaking!!

Amazon ቲክቶክን ለመግዛት ጫራታ ማስገባቱ ተገለፀ።

በአሜሪካ ውስጥ ለ1 ቀን ተዘግቶ የነበረው TikTok ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን በመምጣታቸው ምክንያት እንደተራዘመ ይታወቃል። በዚህ ጊዜም TikTok ለአሜሪካ ዜጋ እንዲሸጥ executive order በመፈረም ቀኑን አራዝመውለት ነበር። ይህም ሊጠናቀቅ የ3 ቀን ጊዜ ብቻ ቀርቶታል።

ይህን እድል በመጠቀም የተለያዩ የአሜሪካ ትልልቅ ድርጅቶች የቻይናውን ድርጅት ለመጠቅለል አሰፍስፈው እየጠበቁ ነው። ከነዚህ መካከል Amazon መጠኑ ያልተገለጸ ገንዘብ አቅርቦ ለመግዛት ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡ Reuters ዘግቧል።


Репост из: የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
የሳይበር ጥቃት በተቋማት ላይ የሚያደርሳቸዉ ዋና ዋና ጉዳቶች


👉መልካም ስም ማጠልሸት፤

👉መሰረተ-ልማት ማዉደም፤

👉ትርፋማነትን ማሳጣት፤

👉ተወዳዳሪነት እና ህልዉና ማሳጣት፤

👉ሚስጥራዊ ሰነዶችን እና ተግባራትን ይፋ ማድረግ፤

👉የእለት ተእለት ተግባራትን ማስተጓጎል ይገኙበታል፤


በALX's 'Pathway Program' አለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ ለማግኘት ይመዝገቡ።
በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ያለው የዚህ ስኮላርሺፕ እድል ተጠቃሚ ይሁኑ።

ለመመዝገብ ይሄንን ሊነክ ይጠቀሙ: https://www.alxafrica.com/join-pathway/

ALX ከ14 ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች በላይ ጋር የትብብር ስምምነት አለው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለመየት ይህንን የቴሌግራም ቻናል መቀላቀል ይችላሉ ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch

ምዝገባው ከ5 ደቂቃ በላይ አይፈጅም!


የኤለን መስክ ካምፓኒ Neuralink በ2025 የመጀመርያውን Brain chip ማየት በተሳነው ሰው ላይ ሊገጥም ነው።

ሙሉ በሙሉ ማየት የተሳነው ይህ ሰው እይታውን ይመልስለታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ መሳሪያ በoptic nerve ችግር ምክንያትና ከተወለዱ ጀምሮ ማየት የተሳናቸውን የእይታ ችግር ይመልሳል ተብሏል።

የአሜሪካ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር መስሪያ ቤት (FDA) ይህን መሳሪያ Breakthrough Device በሚል የመዘገበው ሲሆን እንዲ መመዝገቡም የተለያዩ ጥቃቅን ሙከራዎችን ካለፈ በኋላ ሙሉ ፈቃድ ሊያገኝ እንደሚችል ይጠበቃል።

✍በዚህ ቴክኖሎጂ ትስማማለችሁ? ለምን?


Репост из: Biruk Afework
✨ "People have their own problems, and you have yours, so you don’t have to tell the world about every single issue that you have because nobody cares. 🤷‍♂️ The same can be said about you; if somebody tries to get you involved in his or her personal drama, you wouldn’t care, right?" - Dara Ly ✨


ስልክ ላይ nanometer (nm) ሲባል ምን ማለት ነው?

የስልክ ማስታወቂያ ላይ ባለ 4,6,8 nanometers processor ሲባል እንሰማለን ታዲያ ይህም የስልኩ performance ላይ ትልቅ ሚና አለው። ነገሩ እንዲህ ነው nanometer ማለት 1 × 10⁻⁹ ሜትር ወይም ከፊቱ 9 ዜሮዎችን ከፊቱ የደረደረ  ሜትር/የልኬት አሀድ ነው። nanometer ብዙ ጊዜ ጥቃቅን  ነገሮች ለመለካት ጥቅም ላይ ይውላል።

እንደ transistor ያሉ በስልካችን chip ውስጥ የሚገኙ components መጠን በnanometer የሚለኩ ሲሆን ይህም  nanometer የነዚህን component size ይገልፃል።

chip ውስጥ የሚገኙት ኮምፖነንቶች መጠን ባነሰ ቁጥር በርካታ component መያዝ ስለሚችል አንድ ስልክ የnanometer መጠኑ ባነሰ ቁጥር ይበልጥ ጥራት ይኖረዋል።

ስልኮች ላይ የሚገኘው የnanometer መጠን ትንሽ እየሆነ በመጣ ቁጥር፦
⚫ጥሩ performance ይኖረዋል።
⚫ይበልጥ battery ቆጣቢ ይሆናል።
⚫ብዙ ሙቀት አይፈጥርም ማለትም የመጋል እድሉ እየቀነሰ ይመጣል።

አዳዲስ የሚወጡ ስልኮች ከ8 nanometer በታች processor ቢኖራቸው ተመራጭ ነው።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
https://www.instagram.com/p/DG0Vra_Tr79/

📥 @topsaverbot

Показано 20 последних публикаций.