የጌዴኦ ዞን ሳኢቴ መምሪያ ኃላፊ የ6ኛ ዙር ኮዲንግ ሰልጣኞችን ጎበኙ።
ዲላ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ዶን ቦስኮ ኢ.ቴ.ማ)
ከተጀመረ ሶስተኛ ወሩን ያስቆጠረው 6ኛ ዙር የኮዲንግ ሰልጣኞችን የጌዴኦ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ #ደረጀ_ሾንጣ በዛሬው እለት በት/ቤታችን በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
የማዕከሉ ኃላፊ እና የስልጠናው መምህር ስለ ስልጠናው ሰፊ ገለፃ የሰጠ ሲሆን አቶ ደረጀም በማዕከሉ ተገኝተው በተማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ ስራዎችን አይተዋል።
በ6ኛው ዙር 31 ወንዶች እና 29 ሴቶች በድምሩ 60 ህፃናት ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የተማሪዎችም የክፍል ደረጃቸው ከ6ኛ እስከ 10ኛ ነው። አጠቃላይ አራት ኮርሶችን በስልጠናው የሚመስዱ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ሁለት ኮርሶችን ጨርሰው አሁን ላይ python basic ኮርስ እየወሰዱ ይገኛሉ። በቀጣይ የድረ ገፅ ስልጠና የሚወስዱ ሲሆን ከስልጠናው ጎን በጎን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በሐምሌ ወር የተጀመረው የ5ሚሊዮን ኮደርስ የኦን ላይን ስልጠና ተመዝግበው የሚወስዱ ይሆናል። በስልጠናውም አለምአቀፉዊ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።
አቶ ደረጀም ስለ ስልጠናው ለተማሪዎች ግንዛቤ የሰጡ ሲሆን ከመምሪያው ባለሙያዎችን በመመደብ ተማሪዎች ድጋፍ እንዲሚያገኙ ለተማሪዎቹ ቃል ገብተውላቸዋል ።
የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።