የውድድር ዕድል ጥቆማ
በኤ.አይ እና ሮቦቲክስ ዙሪያ Presidential African Youth in AI and Robotics Competition የተሰኘ አፍሪካዊ ውድድር ተሰናድቷል።
በ12 ዘርፎች የሚደረገው ውድድር እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ለሆኑ አፍሪካውያን ወጣቶች ብቻ የቀረበ ሲሆን አሸናፊዎች የሚጋሩት 120 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡
ለውድድር የሚሆን ስራ ለማቅረብ እስከ ጁን 13፤2025 ድረስ እንደሚቻል በውድድሩ ድረ-ገፅ ተገልጿል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ በዘርፉ ልምድን ያካበቱ አፍሪካዊያን የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ጥሪ እየተደረገ ይገኛል።
Presidential African Youth in AI and Robotics Competition እ.ኤ.አ በ2024 ጅማሮውን ያደረገና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሁነት ነው።
የዘንድሮው ውድድር በአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ፣ በደቡብ አፍሪካ መንግሥት እና ኤሊቬት ኤ.አይ አፍሪካ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የመወዳደሪያ መስፈርቶችን እንዲመለከቱ እና በውድድሩ እንዲሳተፉ እንጋብዝዎታለን።
https://ele-vate.co.za/african-youth-in-artificial-intelligence-and-robotics