Репост из: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 6 | #ቅድስት_አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ ነው፨
ድርጣድስ እሷን ማግባቱ ባልተሳካ ጊዜ አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። በኋላም ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት ቀየራቸው።
የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራዕይ "ጎርጎርዮስን ለ15 ዓመት ከተጣለበት ጉድጓድ ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸውና አወጡት።
ቅዱሱ እንደ ወጣ ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ቤቱን ፈወሳቸው፤ ክርስቲያን አደረጋቸው።
✨ ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።
የሰማዕቷ ቅ/አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።
ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን #ቅድስት_አጋታን ልናስባት ይገባናል። እሷም እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጎኗም ትቆምላት ነበር። ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። አብራትም ተሰይፋለች።
🌿
#ቅዱስ_አባ_አብርሃም እና #ስምዖን_ጫማ_ሰፊው
አባ አብርሃም በተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ግዝቱ የተጻፈለት አባት ነው። ካሊፋው በቂም ተነሥቶ "ወንጌላችሁ ተራራን ተነቀል ብትሉት ይነቀልላችኋል ይላልና አድርጉና አሳዩኝ" ብሎ አዘዘ።
አባ አብርሃምም ለ3 ቀን ከለቅሶ ጋር ምህላ ቢይዝ እመቤታችን ተገልጣ ወደ ስምዖን ላከችው።
ሕዝቡ በአንድ ጎን ካሊፋው በተራራው ሌላ ጎን ሆነው ሳይተያዩ ቆሙ። ቢጸልዩ በተራራው የተሸፈኑት እስኪተያዩ 3ቴ ተነቅሎ ተንሳፈፈ። ዛሬ መታሰቢያቸው ነው።
t.me/Ewnet1Nat