◦◆◦
እውነተኞቹ ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆችና መጪው ዕጣቸው፨
◦◆◦
ቀንና ጊዜ ባለፈ ቁጥር ሥጋ ለባሽ በመከራ ክብደት ይደክማል፡፡ ኃያል ጌታ ግን ለበረከቱ፣ ለምሕረቱ ያተማቸውን ልጆቹን ያጸናል፡፡ የሰጠውን ( የገባውን) ቃል ኪዳን ያከብራል፡፡
ሰው በድካም ዝሎ የተገባለትን ተስፋ ሁሉ ይተዋል፡፡ በብርቱ ድካም ዝሎ ይወድቃል፡፡ ልዑል ግን ያኔ ድካሙን ሁሉ ከድኖ፣ አድሶ፣ በብርታት ሞልቶ በደስታ እንዲቦርቅ ያደርገዋል፡፡የታመንበት የሠራዊት ጌታ ሁሌም እስከ ዘለዓለሙ የታመነ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፍቅሩ፣ መታደጉ፣ በረከቱ ልቡን የሞላው ዳዊት እንዲሁ አለ፦
እግዚአብሔር ወገኖቹን እንደ አይን ብሌን ይጠብቃቸዋል፡፡ በማንኛውም የዲያበሎስ ዘዴ ይወድቁና ይጠፉ ዘንድ በፍፁም አይፈቅድም፡፡
ወገኔ የልዑል ልጅ፤ የቅዱሳን የከበሩት መላእክት ልጆች ብዙ ብትሰቃዩም ይድረሳችሁ የተገባችሁን ነጭ ልብስ ለበሳችሁ፡፡አገራችን ኢትዮጵያ ልዑል ዙፋኑን የሚዘረጋባት፣ ልጆቹን እንቁዎቹን በዙፋኑ የሚያኖርባት፣ ድንግል ልጆችዋን በበረከቷ፣ በፍቅሯ የምታረሰርሳት፣ ኢትዮጵያ ቅዱሳን የከበሩት መላእክት ዙሪያዋን በእሳት አጥረው የሚጠብቁአት፣ የሚባርኳት ኢትዮጵያ፣ የፀናችው አንዲቷ የተዋሕዶ እምነት እንደፀሐይ የምታበራባት ኢትዮጵያ ለልዑል የሰራዊት ጌታ ሌትም ቀንም ለክብሩ ለስሙ ምስጋና እንደጅረት የሚፈስባት ድንግልና ቅዱሳን የከበሩት መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማእታት፣ ነቢያት፣ሐዋርያት፣ ስማቸው የሚከብርባት፣ የሚመሰገኑባት ኢትዮጵያ በክብሯ ጥግ ማንም የማይደርስባት የእግዚአብሔር የስስት ልጁ ናት፡፡ከዚህ ድንቅ አገር የተፈጠራችሁ፣ ለአባታችሁ ለልዑል፣ ለእንቁዋ ለአገራችሁ ኢትዮጵያ ዋጋ ከፍላችሁ በጭንቅ እዚህ ለደረሳችሁ
ወገኖቼ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በእምነት ድሉን ተቀዳጅታችኋልና!◆
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ◆