Репост из: ዓለም ከመልእክታቱ አንፃር...
🟢 🟡 🔴
ታኅሣሥ 8 ልደታቸው የሆኑ፦
🍀 #አባ_ሙሴ_ዘድባ ጽንሰታቸውን ቅዱስ ሩፋኤል መጋቢት 8 ቀን ሲያበሥር ልደታቸውን ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ታኅሣሥ 8 ቀን የመወለዳቸውን ብሥራት ተናግሯል፡፡ ሲወለዱ ሚካኤል ወገብርኤል በሰው አምሳል ተገልጠው "የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ" ብለው ስም አወጡላቸው።
የአቡነ ሙሴ አባታቸው ዮስጦስ ለሐዋርያው ናትናኤል አጎቱ ነው፡፡ እናታቸው ጵርስቅላ ጌታችን በሠርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን የለወጠለት የዶኪማስ ልጅ ናት።
በተወለዱም በ40ኛ ቀናቸው ከተጠመቁ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል አቅፎ ይዟቸው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ አቁርቧቸዋል፡፡
🍀 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡
በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡
🍀 #ቅዱስ_አባ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው።
የሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አጎት ናቸው። በድሏቸው ራሱን ያጠፋውን መነኰስ እና ከ700 በላይ የሆኑ ዐመፀኛ መነኰሳትን ለዓመታት አልቅሰው ከሲዖል ያስወጡ ደግነታቸው የበዛ አባት ናቸው።
🍀 #ቅድስት_እንባ_መሪና በዘመነ ጻድቃን በምድረ ግብጽ ተወለደች፣
◦ ከአባቷ ጋር መንና ወደ ወንዶች ገዳም የገባች፣ ወንድ መስላ የወንዶችን ቀኖና በምንኩስና የተቀበለች፣ ያለ አበሳዋ (ወንድ መስላቸው) "ዝሙት ሠርተሻል" ተብላ ወደ በርሃ የተባረረች፣ ያልወለደችውን ልጅ ያለ በደሏ ተከሳ በትዕግሥት ያሳደገች፣
◦ ያለ ምግብና ውሃ ለ3 ዓመታት የተሰቃየች፣ ብርድና ፀሐይ የተፈራረቀባትና፣ ስታርፍ ክብሯ የተገለጠላት ቡርክት እናት ናት።
✨ በዚህች ቀን ዕረፍታቸውን የምናከብርላቸው፦
🌿 #ቅዱስ_አባ_ሳሙኤል_ዘቀልሞን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ደብረ ቀልሞን የነበሩ፣ ከዓበይት ጻድቃን የሚቆጠሩ፣
✨ ትእዛዝ ያላከበረ መልአክ አማልደው ክንፈ ረድኤቱ እንዲመለስ ያደረጉ፣ መልአክን እንኳ ማማለድ የቻሉ አባት ናቸው።
🌿 #ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሶርያ ደማስቆ የተነሣ ሲሆን፣
◦ ስለ ሥዕለ አድኅኖ ክብር ከነገሥታቱ ዘንድ የተዋጋ፣ በጦማር (በደብዳቤ) ለዓለም የሰበከ፣ ስለ እመቤታችን ተናገርክ ብለው ቀኝ እጁን የቆረጡት፣ እመ ብርሃን ግን እንደ ገና የቀጠለችለት፣
◦ ከ10ሺ በላይ ድርሳናትን የደረሰ፣ ከዐበይት ሊቃውንት የሚቆጠር ቅዱስ አባት ነው።
🌿 #አቡነ_ተክለ_አልፋ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያ የተነሡ ሲሆኑ፣
◦ ደብረ ድማሕን / ዲማን (ጎጃም) የመሠረቱ፣ በፍጹም ተጋድሎ የኖሩ፣ ምድረ ጎጃምን በስብከተ ወንጌል ያበሩ፣
◦ በሊቅነታቸው የተመሠከረላቸው፣ #መልክአ_ኢየሱስን እንደ ደረሱ የሚነገርላቸው፣
◦ ብዙ ተአምራትን የሠሩ (ዛሬም ድረስ የሚሠሩ)፣ ለሃገራችን ትምክህት የሆኑ ታላቅ ሐዋርያዊ አባት ናቸው።
🌿 #አቡነ_ገብረ_ማርያም በ16ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ኢትዮጵያ የተወለደ፣ ስም አጠራሩ ያማረ ሲሆን፣
◦ ዛሬ እናንተና እኔ ለምናደርገው የቅዱሳን መታሰቢያ መሠረት የጣለ፣ በዓመቱ የሚከበሩ ሁሉን ቅዱሳን የሚዘክር፣ 365ቱን ቀናት በምጽዋት የተጠመደ፣ የነዳያን አባት የሆነ፣
◦ በዓፄ ልብነ ድንግል ግራኝ አህመድ መምጣቱን ሲሰማ ያልደነገጠ፣
◦ ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፍሎ፣ ነጭ ልብስ ለብሶ ገዳዮቹን የጠበቀ፣ የግራኝ ወታደሮች የሰየፉትና ሞገስ የሆነን አባት ነው።
🌿 #ቅዱስ_አባ_ኤሲ በዘመነ ሰማዕታት በግብጽ (ቡጺር) ከደጋግ ክርስቲያኖች ተወለደ።
◦ ከልጅነቱ ጀምሮ ዓለምን የናቀ፣ በወጣትነቱ የነዳያንና የእሥረኞች አባት የተባለ፣ ቅድስት ቴክላ የተባለችና እመቤታችን የምታነጋግራት እኅት የነበረችው፣
◦ ቅዱስ ጳውሎስ ከሚባል ባልንጀራው ጋር ሰማዕታትን በመንከባከብ ያገለገለ፣ በመንፈሳዊ ቅናት ከጳውሎስና ቴክላ ጋር ለሰማዕትነት የቀረበ፣ እጅግ ብዙ መከራዎቸን የተቀበለ፣
◦ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሱርያል ወደ ሰማይ አሳርጎ ክብረ ቅዱሳንን በተለይም የሰማዕታትን ክብርና መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሰዎች የሚጠብቃቸውን ክብር ያሳየው ሰማዕት ነው።
[ቅዱስ ሱርያል በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው።]
🌿 #ቅድስት_በርባራ እና #ቅድስት_ዮልያናም ሰማዕትነትን ተቀበሉ።
✨◦✨◦✨
T.me/Ewnet1Nat